እሑድ 7 ሴፕቴምበር 2014

‹‹ይድረስ ላንቺ›› ተፃፈ ከስድስተኛ ተከሳሽ - በዘላለም ክብረት


ወዳጄ ልቤ ከቶ እንደምንድን ነሽ? እውን እኔና አንቺ በአለም ስንኖር ሌላ የመገናኛ ዘዴ አጥተን ወደ snail mail እንመላለሳለን ብለሽ አስበሽ ታውቂያለሽ? ለማንኛውም እንዲህ ሆነ፡፡ ጥጋበኛ ሰው ያስቀናኝ ጀምሮልሻል፣ ጥጋበኛ እንዲህ የሚለው ትዝ አለኝ፡፡

‹‹ ….ደብዳቤ ቢጽፉት እንደ ቃል አይሆንም፣
እንገናኝ እና ልንገርሽ ሁሉንም….››

የደላው! ቢያሻው በደብዳቤ፣ ሲፈልግ በአካል እያማረጠ እኮ ነው፡፡ ለእኔ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ሁለቱም ቅንጦት ነው (ወይ ደብዳቤው አይደርስሽም ወይም አንቺን ማየቴ ሊገደብ ይችላል)፡፡ ቆይ ትንሽ የጎን ወሬ ላዋራሽና ምክንያቱን እነግርሻለሁ፡፡ ‹‹አንቺ›› ተብለሽ በዚህ ደብዳቤ ስለተጠቀስሽው ‹‹አንቺ›› ይሄን ደብዳቤ ለሚያነቡ ወዳጆች የዕምነት ክህደት ቃሌን በትንሹ ላስፍር፡፡

እመቤት ሲልቪያ ፓንክረስት የኢትዮጵያ ፍቅረኛ (Ethiopian by choice) ዱቼ ሞሶሎኒ እትዮጵያን በወረረ ጊዜ፤ ወራሪው ሃይል በመላው ኢትዮጵያ ‹‹ የኢትዮጵያን ስም እያነሱ መፃፍ ክልክል ነው›› የሚል ያልተፃፈ አዋጅ አውጆ እንደነበር ይነግሩናል፡፡ በዚህም ምክንያት ፀሀፍቱና አዝማሪያኑ ስውር መጠሪያ መጠቀም ስላስፈለጋቸው እስከ ዛሬ ድረስ ተወዳጁ ሕዝባዊ ዘፈን አንቺ ልጅ አንቺ ልጅ እንደ ስውር የፍቅር ዘፈን ተበርክቷል፡፡ በዘፈኑ ‹‹አንቺ ልጅ ›› የተባለችውም ኢትዮጵያ ናት፡፡ እኔስ በዚህ ዘመንይድረስ ለባለ ታሪኩይድረስ ለባለ ንብረቱ›… እንደሱ የሀዘን ደብዳቤ ርእስይድረስ ለኢትዮጵያበማለት ፋንታይድረስ ለአንቺለማለት ስውር መጠሪያ ተጠቅሜያለሁ? በፍፁም! ጌቶች እንደሚሉት ሕገ መንግስቱ የመናገር ነፃነቴን ሙሉ ለሙሉ አስከብሮልኛልናi
ቧልቱ ይቆየንና በዚህ ደብዳቤ ርዕስ ዙሪያ ያለማንም አስገዳጅነት የእምነት ክህደት ቃሌን ላስፍር አንቺ የተባለችው ኢትዮጵያ አይደለችም፡፡አንቺየኔዋ ሀቢቢ ግን ባለሽበት ይድረስሽ፡፡ ውዴ እንግዲህ በዚህ ደብዳቤ ያለፈውን እያነሳሁ እነግርሻለሁ፡፡ወይ ትስቂያለሽ (ሳቅሽ እንዴት ያምራል?) ወይ ደግሞ ታዝኛለሽ (እኔን!)

ይህንን ደብዳቤ የመፃፍ መብት
እነሆ ላንቺ ስለሆነው ሁሉ ላጫውትሽ ስጀምር፤ በመነሻው ያሰብኩት ነገር ይሄን ደብዳቤ የመፃፍ ሕጋዊ መብት አለኝን? የሚለውን ጥያቄ ነው፡፡ ለዚህም መነሻዬ አሁን ያለሁበት ሁኔታ ነው፡፡ በመጀመሪያሕገ-መንግስታዊ ስርአቱንና ሕገ-መንግስቱን በሀይል ፣በዛቻና በአድማ ለመናድ በመምከር/ በመናድወንጀል ተጠርጥሬ የታሰርኩ ቢሆንም፤ በታሰርኩ 23ኛው ቀን ወንጀል ወንጀልን፤ ጥርጣሬ ሌላ ጥርጣሬን እየወለደ የተለያዩ የሽብር ተግባራትን ለመፈፀም ለማሴርና ለማነሳሳት ወንጀል ተጨማሪ ጥርጣሬ በፓሊስ ዘንድ በማሳደሬ የክፋት ልኬ ከፍ ያለ ሲሆን፤ በመጨረሻም ሕገ-መንግስቱን እንደ እያሪኮ ግንብ ለመናድ በመሞከር፤ ሕብረተሰቡን ደግሞ ከሚተነፍሱት የሰላም አየር ለማቆራረጥ ከማሰብ የተለያዩ የሽብር ተግባራትን ለመፈፀም ሲንቀሳቀስ ተይዟል በሚል ወንጀሎች ተከስሼ በማረፊያ ቤት እገኛለሁ፡፡ ይሄን ሁሉ የምነግርሽ አንቺአዲስ ነገር ነው በማለት አይደለም፡፡ ይልቁንስ ያለሁበት የእስር ሁኔታ ደብዳቤ ካንቺ ጋር እንዳልፃፃፍ ይከለክለኛልን?  የሚለውን ለማስረዳት በማሰብ ነው፡፡

መቼም አሁን ያለሁበት ሁኔታ ተገቢ ነው ብዬ ባላምንምዋስ ጠበቃዬ ነውናስለመብቴ ስናገር ያን የፈረደበት ህግ መጥቀሴ አልቀረም፡፡ ታዲያስ በእስር ላይ ያለ ሰው ከወዳጁና በሕይወቱ ጋር ደብዳቤ ሊፃፃፍ ምን ገደብ አለበት? ይላል ስል፤ ስለፌደራል ታራሚዎች አያያዝ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 138/1999 በአንቀፅ 18 ላይ "ታራሚዎች (ተጠርጣሪዎች) ከማረሚያ ቤቱ (ከማረፊያ ቤቱ) ውጭ ካሉ ሰዎች ጋር መፃፃፍ ይፈቀድላቸዋል፡፡ ሆኖም ለጥበቃ ስራ ተቃራኒ የሆነ ተግባር እንዳይፈፀም በፅሁፎቹ ላይ ቁጥጥር ይደረጋል" በማለት የኔና አንቺ ደብዳቤ መፃፃፍ በሕግ የተፈቀደ ነገር እንደሆነ ደንግጎልናል፡፡ አሜን(እንዲያው ይሄ ልጅ አሁንስ ተስፋዬ.. ማነው ? ሕጉ አይደለምን... የሚል የጅል ዘፈኑን አላቆምም እንዴ? ብለሽ እንደማታሾፊብኝ እምነቴ ነው ጓድ ሌኒን በዛች የፒተርስበርግ እስር ቤት ውስጥ ደብዳቤ መፃፃፍ አትችልም ተብሎ ተከለከለ እርሱ ግን Russia Social Democratic Party ፕሮግራም መፅሀፍ ውስጥ በየመስመሮቹ መሀል Invisible Ink በመፃፍ ታሪክ ስራ፡፡ እነሆ እኔ ግን በትናንት ሌኒኒስቶች (ፋና) በዛሬ አሳሪዎቻችን መልካም ፈቃድ ደብዳቤ የመፃፃፍ ሕጋዊ መብቴ ተከብሮልኝ ይሔው በነጩ ወረቀት ላይ እንደ ሕዳሴው ባቡር እፈነጭበታለሁ፡፡

እንዲህ ሆነልሽ
አበባዬ- አፄ ሀይለስላሴ ከማንኛውም ባለስልጣን በሕይወት ዘመናቸው የበለጠ የቀረቧቸው የነበሩት 1934-1948 ድረስ 14 ዓመታት በፅህፈት ሚንስትርነት ያገለገሏቸውን ፀሀፊ ትዕዛዝ ወልደ ጊዎርጊስ ወልደ ዮሀንስን እንደ ነበር ነግሬሻለሁ? ወዳጅነትና ፍቅር ያልፋልና ሀይለስላሴና ወልደ ጊዎርጊስ ተጣሉ፡፡ የአፄ ሀይለስላሴ መንግስት መፅሀፍ ፀሀፊ አቶ ዘውዴ ረታ የወልደጊዎርጊስን መጨረሻ ሲተርኩ፡፡

‹‹ ፀሃያማው ሚያዚያ 17/1948 ቀን ወልደ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሀንስ እንደ ሌሎቹ ቀናት ብሩህ ሁና ነበር የነጋችው፡፡ ብሩህ ሁና እንደምታመሽም አልተጠራጠሩም ነበር፡፡ ምን ያደርጋል! ያች ክፉ ሰኞ የወልደጊዎርጊስ ከፍተኛ ስልጣን መጨረሻ ሆነች፡፡ በእኩለ ቀን ገደማ ቤተ መንግስት ተጠርተው ከፅህፈት ሚንስተርነታቸው ተነስተው የአሪሲ ጠቅላይግዛት ደረሳቸው››
(መፅሀፉ አጠገቤ ስለሌለ ቃል በቃል አልጠቀስኩም)

ወልደጊዮርጊስ ተሽረው ከቤተ-መንግስት እንዲርቁ የተደረገበት ምክንያት የሀይለስላሴን ወንበር በሰዒረ መንግስት ለመገልበጥ አስበዋል በሚል ምክንያት ነበር፡፡ወልደጊዎርጊስን እዚህ ጋር ማንሳቴ የሚያዚያ 17 ስለት እኔም ጋር በመድረሷ ነው፡፡ ውዴ! የእኔዋን ሚያዚያ 17/2006 . ውሎ እንደ ዘውዴ ረታ ስተርክልሽ ይሔን መሳይ ይሆናል፡፡

 
‹‹ ፀሃያማዋ ዓርብ ሜያዚያ 17/2006 . አጀማመር እንደ ወትሮው አልነበረም፡፡የጠዋት ትምህርት ክፍለ ጊዜ እንዳይረፍድብኝ እየተቻኮልኩ ወደማስተምርበት (የመጨረሻ ክላስ ነበር) አምቦ ዩንቨርሲቲ ስሄድ፤ ተማሪዎች አዲስ የተዘጋጀውን የአዲስ አበባ ከተማ መሪ እቅድሕገ-መንግስታዊ አይደለም በሚል መነሻ የተለያዩ መፈክሮችን እያሰሙ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው ነበር፡፡ ሰልፉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተካሂዶ እንደተጠናቀቀ በሰልፍ ምክንያት የቀረውን የመጨረሻ ክላስ ሚያዚያ 18/2006 . ለማካሄድ ተማሪዎቼ ጋር ቀጠሮ ይዤ ብለይምሰው ያቅዳል እግዜር ይስቃልእንደሚባለው ሆነና በዛች ሚያዚያ 17/2006 . ማምሻ ላይ እንደ ወልደጊዎርጊስ ወልደ ዮሃንስየመንግስትን ዙፋን በሕዝባዊ አመፅ ልትነጥቅ አሲረሀልበሚል ክስ በቁጥጥር ስር እንደዋልኩ የደህንነት ግሪሳዎች (8 ወይም 9 የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አባላት ) አበሰሩኝ፡፡ 

 ነገሩ ብዙም አልገረመኝም፡፡ ትንሽ ያበሳጨኝ አቶ ዘላለም ለጥያቄ ስለምንፈልጎት አዲስ አበባ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ዘርፍ (ማእከላዊ) ነገ ጠዋት 3 ሰዓት እንዲገኙ ብለው በስልክ ቢጠሩኝእሺ ነገ ሶስት ሰአት ላይ ክላስ አለኝ ከክላስ ወደ 9 ሰዓት አካባቢ አመጣለሁብዬ የምቀርበውን ሰው ይሔን ሁሉ ሀይል ከሁለት መኪና ጋር በመመደብ ላከበረኝ መንግስቴጉዳትባሰብኩ ግዜ ነው፡፡ ላክባሪዬ ውለታ መላሽ ያርገኝ i

ዓለሜ- ደብዳቤዬን እያነበብሽው እንደሆነ ተስፋ አለኝ፡፡ በቁጥጥር ስር ውሏል የምትለው ሀረግ ድሮም ትንሽ ፈገግ ታደርገኝ ነበር፤ አሁን ደሞ እኔን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከአዲስ አበባ የመጣው የደህንነት ቡድን መሪ የመሰለኝ እድሜው ትንሽ ገፋ ያለ ሰው አንድ ሶስቴ ስልክ እየደወለ (ለማን ይሆን) ‹በቁጥጥር ስር አውለነዋልእያለ መልክት ሲያስተላልፍ ስሰማ ፈገግ ማለቴ አልቀረም፡፡ ሀሳቤ ልቤ ይሄውልሽ ከስራ ቦታዬ  ‹ሀገር ሰላምሕዝባዊ አመፅ ለመቀስቀስ አስበሃል በሚል ጥርጣሬ በቁጥጥር ስር የዋልኩት እንዲህ እንደገለፅኩት ነበር፡፡ ከሚያዚያ 17/2006 -ሀምሌ 11/2006 . ያሉት 84 ቀናት የተደጋገሙና ሕይወት አልባ በመሆናቸው እንዲሁ ከማሰለችሽ 5 ሁነቶችን ልፃፍልሽና ዘና በይ፡፡ ከሁነቶቹ በፊት ግን ስለ 84 ቀናቱ አጭር መግለጫ ልስጥሽ፡፡

የመጀመሪያዎቹን 75 ቀናት በፌደራል ወንጀል ምርመራ ዘርፍ (ማዕከላዊ) ጥብቅ ጥበቃ ክፍል (Siberia) ውስጥ 5 ቁጥር የተባለ 4 ሜትር 5 ሜትር የሆነችና 5 ፍራሾችን በምትይዝ ክፍል ውስጥ ከረምኩ፡፡ ክፍሉ የተፈጥሮ ብርሀን በምንም አይነት መንገድ (ቀንን ጨምሮ) የማይገባበት ሲሆን፣ 24 ሰዓታት የመብራት ብርሀን ይበራበታል፣ መብራት ሲጠፋ በጄኔሬተር ሀይል ይተካል፡፡ ጄኔሬተሩ ነዳጅ ሲጨርስ ደግሞ ቀንም ሆነ ማታ ጨለማ ነው ባትሪ፣ ሻማ፣ ማንኛውንም አይነት ሰዓት መያዝ አይቻልም፡፡ ጠዋት 12 ላይ 10 ደቂቃ ማታ 10 ሰዓት አስከ 12 ሰዓት 10 ደቂቃ ሽንት ቤት ለመጠቀም የክፍላችን በር የሚከፈት ሲሆን፤ በቀን ውስጥ 15 – 20 ደቂቃ ለሚሆን ጊዜ ደግሞ ከክፍላችን በየተራ ወጥተን ነፋስ/ፀሀይ እናየለን፡፡ ከዛ ውጭ በቀን ውስጥ 23 ለሚበልጠው ሰዓት የክፍሉ በር ዝግ ሲሆን ጮክ ብሎ ማውራትና መዝፈንም ቅጣት ያስከትላል፡፡

ወዳጄ በነዚህ 75 ቀናት ስንትአሸባሪወዳጆችን አፈራሁ መሰለሽ፡፡ መንግስቴ 15 እና 14 ዓመት ልጆችን በአሸባሪነት ጠርጥሮ እንደሚያስርም ለመረዳት ችያለሁ፡፡ አብረውኝ በእስር የነበሩት ወዳጆቼ ጥርጣሬ አጅግ የተለየ ነው፡፡ ከአል-ሸባብ አስከ ኦብነግ እስከ ኦነግ እስከ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ሕዝቦች ነፃ እውጭ ግንባር እስከ አቂዳ(አዲስ የሽብር ቡድን)… ስቃይን መማር ጥሩ ነውና ሁለት ለሚሆኑ ቀናት ብቻዬን በመታሰሬም solitary confinement experience ለማድረግታድያለሁ፡፡ በርግጥ ብቻዬን ታስሬ ነበር ከምል ካንቺ ሀሳብ ጋር ታሰርኩ ብል ይቀለኛል፡፡

አምስቱን ሁነቶች ዘንግቼ ስለ ስቃዬ ተንዛዛሁብሽ ይሆን? ለዚህ ተግባሬ በእስረኛ ቋንቋተፀፅቻለሁ፡፡ በቃ ወደ ጉዳዮቹ፡፡ ከዚህ በታች የምገልፃቸው ሁነቶች 84 ቀናቱ የእስር ወቅት (የምርመራ) ጊዜ ምን እንደሚመስል እንደነበር ያስረዱሻል ብዬ አስባለሁ፡፡ (ሁሉም በእውነት እኔ ላይ የደረሱ ጉዳዮች ናቸው)

1.    ተማሪዎቼን እንዳላበላሻቸው በማሰብ በቁጥጥር ስር ስላዋለኝ አመሰግናለሁ
ሚያዝያ 17/2006 ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ ከምኖርበት አምቦ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ከደህንነቶች ጋር በቤት አውቶሞቢል እየተጓዝኩ ነው፡፡ አንድ ልጅ እግር ደህንነት ጠየቀኝ
‹‹
ዘላለም የህግ መምሕር ነህ አይደል..››
            እኔ አዎ
            ደህንነቱ  "ስንት ጠበቆች ዳኞች ማፍራት ሲጠበቅብህ አንተልማቱን ካላደናቀፍኩ ማለትህ እጅግ ያሳዝናል፡፡ ለማንኛውም እንኳን ተማሪዎቹን ሳታበላሻቸው በጊዜ በቁጥጥር ስር ዋልክ፡፡ ኧረ                  ለመሆኑ ከውጭ ስንት ሽህ ደላዮችን አግኝተሻል? Any way በልማታችን ቀልድ የለም" አለኝ፡፡ (እኔም ባስተማርኩባቸው 4 አመታት ስንት ተማሪዎችንእንዳበላሸሁ እያሰብኩና ልማታችን                  በወለደው የአስፋልት መንገድ ብዬ ከምሽቱ 350 ላይ ማዕከላዊ ከቸች፡፡

2.   አላማችሁ ምንድን ነው?
እመቤቴ - መንግስት ሕዝባዊ አመፅ ለመቀስቀስ አሲራችኋል፤ ለዚህም በቂ ማስረጃ አለኝ በማለት ያሰረን ቢሆንም መንግስት ሀሳቡ እውነት ይሆንለት ዘንድ የእኛንአዎ አሲረናል የሚል መልስ በማባበልና በሀይል ለማግኘት ከመሞከር ውጭ ሌላ ያቀረበው አንዳችም ማስረጃም ሆነ መረጃ(በጠ/ሚንስትሮች ቋንቋ) አልነበረም/የለምም፡፡ ለዚህም ይመስላል በማእከላዊ የቆየሁባቸው ቀናት ምርመራው በሙሉአላማችሁ ምንድን ነው? በሚል ሕይወት አልባና አሰልቺ ጥያቄ የተሞላው፡፡ እኔም የዚህ ጥያቄ ሰለባ ሁኜ ከረምኩልሽ፡፡ እንዲህ ላጫውትሽ፣
           
መርማሪ ፖሊስ (በተደጋጋሚ) - እንደ ዞን 9 አላማችሁ ምንድን ነው?
           እኔ ዓላማችን ግልፅ ነው፡፡ ማንም ብሎጋችንን የተመለከተ ሰው በቀላሉ ሊረዳው ይችላል፡፡ባጭሩ የተለያዩ ተረኮችን የሚያስተናግድ እና ሕብረተሰባዊ ተዋጾን የሚያሳድግ ፕሮፋይል ነው፡፡
           መርማሪ ፖሊስ እሱ ሽፋን ነው፤ እውነተኛ ዓላማችሁን ተናገር?
           እኔ ከዚህ የተለየ አላማ የለንም!

መርማሪ ፖሊሱ እንድንመልስለት የሚፈልገውከበላይ አካልይዞ እንዲመጣ የታዘዘውን መልስ፤አላማችን እንደ ጭቃ ተረግጦ፤ እንደ ገል ተቀጥቅጦ የሚገኘውን ጭቁን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከተጫነበት ቀንበር ነፃ ማውጣት ነው፡፡ ለዚህም መሳካት ሕዝባዊ አመፅ ማደራጀትን እንደ ዋነኛ ዓላማ አድርገን ነው የተቋቋምነው፡፡
ሲሆን ይህ ደግሞ ከአላማችን ጋር የማይገናኝ መንግስታዊ ፍላጎት በመሆኑ እንዲህ አይነት መልስ ከእኔ ማግኘት እንደማይችል የተረዳው መርማሪ በተደጋጋሚ አስብበት በማለት ይሰናበተኝ ነበር፡

3.   ከመርማሪዎች ጋር የነበረኝ ቆይታ
የእኔ ፅጌሬዳ አላማችን እንደ ቡድን ባይጠይቁኝ ኑሮና የግል ዓላማዬን ቢጠይቁኝ አላማዬአንቺእንደሆንሽ ከመናገር ወደኋላ እንደማልል ታውቂያለሽ አይደል? የሆንሽአሸባሪነገር፡፡ Any way ምርመራዬ ቀጥሎልኛል፡፡ ሁለት መርማሪዎች እየተፈራረቁ ገራሚ ገራሚ ጥያቄዎችን እየጠየቁኝ ነው፡፡ እነሆ
         መርማሪ ፖሊስ ከአለም መሪዎች ማን ማንን አግኝተህ ታውቃለህ?
         እኔ ማንንም
         መርማሪ ፖሊስ እኛ እኮ ያለመረጃ አይደለም እየጠየቅን ያለነው፡፡ ጉድ ሳይመጣብህ ብትናገር ይሻላል፡፡
         እኔ እስኪ አስታውሱኝና ምን እንደተነጋገርን ልናገር፡፡ በርግጥ ባለፈው የኔልሰን ማንዴላ ማስታወሻ ፕሮግራም አፍሪካ ህብረት በተከበረበት ወቅት / ሀይለማርያም ደሳለኝ አግኝቻቸዋለሁ፡፡ ሌላ         የማስታውሰው የለም፡፡
        መርማሪ ፖሊስ፡ ህም! እሺ ዘንድሮ ኦባማ ፊት ንግግር ለማድረግ ከተመረጡ 3 ኢትዮጵያውያን አንዱ አንተ አይደለህም? አሜሪካ አፍሪካ ጉዳይ ምን አግብቷት ነው፡፡ ወጣት አመራሮች ምናምን             እያለች የምታሰለጥነው?
        እኔ ‹‹እንዴ ኦባማ ፊት ንግግር ነው ያልከኝ? ድንገት ከታሰርኩ በኋላ ተመርጬ (በማሾፍ ድምፀት) ከሆነ አላውቅም፡፡ወይ በስም መመሳሰል ሊሆን ይችላል፡፡ አሜሪካ በአፍሪካ ጉዳይ ምን አግብቷት           ነው? ላልከኝ ግን ወጣቶችን Empower ማድረግ ችግር ያለው አይመስለኝም ደግሞ በረሀቡም በድርቁም ጊዜ ርዳታ የምታደርገው እኮ አሜሪካ ነች፡፡ ምን አግብቷት ነው የምትረዳው አይባልም               መቼም?!››
        መርማሪ ፖሊስ አሁን ዘመኑ የልማት ነው፤የምን ረሀብ ነው የምታወራው? በል ተወው፡፡

            (‹
ፈሪ ውሃ ውስጥ ያልበዋልሰምተሻል ውቤ? መንግስቴ ብቻውን እየሮጠም ፍርሃቱና ስጋቱ ብዛቱ፡፡ የሚቆጨኝ ነገር ከዓለም መሪዎች ማን ማንን አግኝተሃል? ‹ስባልከሲሪላንካ ፕሬዜዳንት ጋር ተገናኝቼ ወደ ደቡብ አሜሪካ ፔሩ በመጓዝ ማቹፒቹን ጎብኝቻለሁ ብዬ ብናገር ኑሮ፤ ክሳችን ላይከሲሪላንካ መንግስት ባገኘው የገንዘብና የመሳሪያ ድጋፍ ወደ ፔሩ በመጓዝ ሕገ-መንግስት እንዴት እንደሚናድ በማቹፒቹ ኮረብታ ስልጠና ወስዶ ተመልሷል፡፡ ለዚህ እንደ ማስረጃ ይሆን ዘንድ ላፕቶፔ ውስጥ የተገኙት 300 በላይ የቼጉቬራ ምስሎችና Machu Pichu: The Mecca of Hippies” የሚል ባለ 22 ገጽሰነድአብሮ ይያዝልኝ ነበር፡፡ ሲያበሳጭ

4.   ‹አሸባሪውገብረሕይወት ባይከዳኝና ሀገሪቱን በሀራጅ የመሸጥ ጉዳይ
ፍቅር አደከምኩሽ አይደል?! ልጨርስ ስለሆነ ትንሽ ታገሺኝ፡ በዛውምፍቅር ታጋሽ ነውየሚለውን Paulian ወንዴነት፤ፍቅር ታጋሽ ናትበሚል ማስተካከያ እንድናርመው፡፡ የዚህ የምርመራ ነገር እኮ አላልቅልኝ አለ፡፡ በእስሬ ወቅት ሌላው በተደጋጋሚ እንዳስረዳ ስጨቀጨቅበት የነበረው ጉዳይኒዮ-ሊብራልነቴና ልማትና ዲሞክራሲ ጎን ለጎን አብረው ይሄዳሉ ማለቴ ነበር፡፡
መርማሪ ፖሊሶቹ እየተቀያየሩ ስለኢህአዴግ የፖሊሲ ትክክለኛነትያስረዱኝነበር፡፡አንተ ምን ጎደለብኝ ብለህ ነው ነጭ አምላኪ የሆንከው ? ትንሽ የተስፋ ጭላንጭል ስናይ አንተና ጓደኞችህ አይናችሁ ለምን እንደሚቀላ እስኪ ንገረን ? ይህች አባቶቻችንበደምና በጾምያቆዩልንን አገር አንተና ያንተ ትውልድ ግን ውበቷ እና ድንቅነቷ ላስጎመጃቸው ነጮች ለመሸጥ መደራደር ጀመራችሁ….” እያሉበባንዳነትሲከሱኝ ከረሙ፡፡ የሀገሪቱ ውበትና የነጮች በውበቷ መጎምጀት ነገር ሲነሳ ጊዜአንቺትስቂ ዘንድ የሚከተለውን አንቀፅ አሻግሬ ታደሰ የተባሉ ፀሐፊ 50 ዓመት በፊትእኔና አንተካሉት ጽሁፋቸው ላይ እጠቅስልሻለሁ

"ኢትዮጵያ እጅግ ያማረች፤ የተዋበች ፤የተደነቀች፤ላያት ሁሉ የምታማልል፤የምታዘናጋ…….ናት፡፡ ዓይኗ የብር አሎሎ መለሎ ከአጥቢያ ኮከብ የተፎካከረ….. ነው፤ አገራችን ኢትዮጵያ ፅጌረዳ መስላ የሰኔን ቡቃያ ትመስላለች፡፡ የመስከረም አበባ ሆና በሩቅ ትስባለች፤የመስህቧ ኃይል ማግኔት ምስጋን ይንሳው፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ ጥርሷ እንደ በረዶ ሆና ለፈገግታ ያህል ትንሽ ከንፈሯን ስትገልፀው እንኳንስ ለሰው ግብዙ መልዓክ ያብዳል፡፡ ኢትዮጵያ ፀጉሯ የሀር ነዶ ነው፤ኢትዮጵያ አጠረች ፤ረዘመች፤ወፈረች፤ብሎ ስለአካሏ መናገር አይቻልም፡፡ እንዲያው ዝም ይሻላል፡፡ በጠቅላላው ኢትዮጵያ ውበቷ ሰነፉን ይገድላል፡፡ ብርቱውን አነሁልሎ ያሳብዳል፡፡ እግዚአብሔር፤ኢትዮጵያን ሲፈጥር በብዙ ተራቋል፤ተጠቧል፤ ውበቷ በሩቅ ይስባል፤ አጥንትም ይሰብራል፤አዕምሮን ይሰውራል፡፡ ይገርማል!" ይላሉ፡፡

 
ምንም እንኳን ውበት እንደተመልካቹ ነው ቢባልም፤ መርማሪዎቹ በዚህ ዓይነት Vulgar Natioanlism ሰክረው እኔና የእኔ ትውልድ ሀገሪቱንበውበቷ ለሰከሩነጮች ልንሸጣት እንደተዋዋልን እየነገሩኝ ነው፡፡ ይገርማል! ዲሞክራሲን ከልማት እኩል ማስኬድ ነውር የለበትም፤ ተገቢም ነው ማለት እንደ አገር ሽያጭ ውል የሚቆጠርበት ብሎምሩቅ አስባ ሩቅ ለማደር እየተጋች ያለችን አገርመንገድ ላይ በጠረባ ለመጣል የተደረገ ሙከራ ተደርጎ የሚወለድባትናአሸባሪየምንሰኝባት፣ለፈገግታ ያህል ትንሽ ከንፈሯን ስትገልጠው እንኳን ሰውን ግብዙን መልዓክ የምታሳብደው ኢትዮጵያ!

ሊቁ ገብረሕይወት ባይከዳኝልማትን ሲተች›  እውቀት በሌለው ሕዝብ አገር መንገድና የምድር ባቡር ቢሰራ ሕዝቡ እንዲደኸይ ያፋጥናል እንጂ አይጠቅመውም፡፡ ጥቅሙ ከርሱ ጋር የሚገበያዩ አዋቂ ሕዝቦች ነው”  በማለትልማት ብቻውን ዋጋ የለውምሲል ይበይናል፡፡ ገብረሕይወት የእኛው ትውልድ አባል ቢሆን ኖሮ  “የኢኮኖሚ እድገቱን በመካድ፤ ሕዝቡ በአዕምሮ መናወጥ ምክንያት የዘረጋነውን የባቡር ሀዲድ ፈነቃቅሎ እንዲጥልና ሌሎች የሽብር ተግባራትን እንዲፈፀም በማነሳሳትወንጀል›” መመርመሩና መከሰሱ አይቀሬ ነበር፡፡
ውዴ! ያንአሸባሪሳቅሽን ሳስብ በፀረ-ሽብር ሕጉ መሠረት ጉዳይሽ ሊታይ ይችላል የሚል ስጋቴ የበዛ ነው፡

5.   ናፍቆቴ ሆይ!
እንዲያው ለዚህ 84 ቀናት ውስጥ የሆንኩትን ሁሉ እንዳልፅፍልሽ እንዳትሰለችብኝ ፈራሁ፡፡ እያንዳንዱን ሁነት Diary መልክ ከትቤ እንዳልክልሽ በነዛ ቀናት ውስጥ ብዕርም ሆነ ነጭ ወረቀት ይዞ መገኘትከፍ ብሎ አንገትን፣ ዝቅ ብሎ ባትንባያስቆርጥም ዛቻና ዱላን ማስከተሉ አይቀርም ነበርና ልከትብ አልቻልኩም፡፡ እንዲሁ በደፈናው ግን አንዳንድ ጉዳዮችን ብዘረዝርልሽ፡
·                      በነዛ ክፉ ቀናት ከምሽቱ 12 ሰዓት እንቅልፍ መተኛትን ለመድኩ፡፡ ይሔም ነገር መልካም እንደሆነ አየሁ፡፡ ምክንያቱም ሌሊት ከእንቅልፍ ተቀስቅሰው ራቁታቸውን ሲደበደቡ አድረው 3 እና 4 ሰዓታት ቆይታ በኋላ በነፍስ ወደ መኝታ ክፍላችን የሚመጡ የእስር ጓደኞቼን  (Cellmates) ስቃይና ሰቆቃ ላለመስማት፡፡
·                      2004 . የፌዴራል ፖሊስ ‘Cyber crime Laboratory’ ተቋቁሟል መባሉን ሰምቼእንግዲህ cyber criminal ሁሉ የት ትገቢ? አለቀልሽ!› ብዬ ነበር፡፡ በጊዜ ቀጠሮ ጊዜ እንደተረዳሁት ደግሞያለችን አንዲት ኮምፒውተር ናት የእነዚህ ልጆች ዳታ በአንድ ኮምፒውተር መርምረን መጨረስ ስላልቻልን የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠንሲባል ነው፡፡ አረ እንዲያውምእስኪ Anti-virus ካለህ ኮምፒውተሬ ላይ ጫንልኝተብዩ ሁሉ ነበር፡፡ለሽብር ተግባራትመመርመሪያ ያልሆነ ‘Cyber crime laboratory’ ለመች ሊሆን ነው?
·                     አንድ ቀኑንና ወሩን በማላስታውሰው ቀን አንድ ጎልማሳ የታሰርንበትን ክፍል አስከፍተው ገቡና እያንዳንዳችን መጠየቅ ጀመሩ፡
-   አንተ ከየት ነው የመጣኸው?› (አንድ ተማሪ ወዳጄን)
-  
 ከሀሮማያ ዩኒቨርስቲ
-  
 አሀ እናንተ ናችኋ…..›
****
-  
 አንተኛውስ ከየት ነው የመጣኸው?!›
-  
 ከወለጋ ዩኒቨርስቲ
-  
 አሁን ኦሮሚያ ብትለማ ምን የሚያስከፋ ነገር አለው?!....›
*****
-  
 አንተስ ከየት ነው የመጣኸው› (እኔን ነው)
-  
 ከአምቦ ዩኒቨርስቲ
-  
 ሕዝቡን እርስ በርስ አጋጭታችሁ ከተማዋን በደም ያጠባችኋት እናንተ….›
-  
 አረ እኔ ከግጭቱ በፊት ነው የታሰርኩት
-  
 በእውነት ነው የምልክ እድለኛ ነህ፡፡ የኦሮሚያን ልማት ተቃወመ ተብለህ በታሪክ አለመስፈርህ በጣም እድለኛ አድርጎሀል፡፡
(
ለመሳቅ ሁላችንም የጎልማሳውን ከክፍል መውጣት እየተጠባበቅን እኮ ነው ውዴ) - ሁሉ ቧልት የሆነበት ሀገር!

በነዚህ ሁሉ የጉድ ቀናት ለምን እንደታሰርኩ ትክክለኛውን ምክንያት የሚነግረኝ አካል ፍለጋ ሁሌም አስብ ነበር፡፡ መታሰሬ ግን አያስገርመኝም፤ አያስከፋኝም! ደስታን በሔድኩበት ሁሉ እፈልጋለሁ፤ የእድል ነገር ሆኖ ደስታም ከእኔ አይርቅም፡፡ ፍቅሬ ለረጅም ዘመናትየሰው የመኖር አላማ ማወቅ ነውየሚለውን Aristotlian (አሪስቶትሊያን) አስተምህሮ በልቤ ይዤ እኖር ነበር፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግንየመኖር ዓላማ መደሰት ነውየሚለው አስተምህሮ በአርስቶትሉየማወቅ ዓላማደባልቄ ይሔው እየተደሰትኩልሽና እያወቅሁልሽ እገኛለሁ፡፡አንችየደስታዬ ምንጭ፡

‘‘Thanks to you….For you exist’
Clézio

ስለክሴና ስለተስፋዬ ሌላ ደብዳቤ እፅፍልሻለሁ፡፡
P.S
አሳሪዬ ሆይ ልብ ይስጥህ!
                                                           
ያንችው ዘላለም
                                                                       
ከብዙ ፍቅር ጋር!


‘‘ከመቃወም ባሻገር በኢትዮጵያ’’ ፪

ሀ. ለድምጽ የለሾቹ ድምጽ ስለመሆን

አንዳንድ ጊዜ በተወሠኑ ጉዳዮች ላይ የሚሠማው ጩኸት በጣም ይገናል፡፡ የጩኸቱ ብርታትም ይሠማል፡፡ የተወሰኑ ጉዳዮች ከሌሎች በተለየ መልኩ ትኩረት ይስባሉ፡፡ እኒህን ጉዳዮች ተጠቅመው የሚያራግቡ በርካታ ፓርቲዎች አሉ፡፡ በተለይ የብሔር፣ የሐይማኖት፣ የግዛትና መሠል ጉዳዮች ምድሩን ለመነቅነቅ ሲቻላቸው ይታያል፡፡ እነዚህ ጉዳዮች በአንድም ይሁን በሌላ ከማንነት ጋር የተያያዘ ስለሆነ ሁሉም የራሱን ጽንፍ ለመያዝ ሲጮህ ይሠማል፡፡ በርካታው ጩኸት ግን ችግሩን ከማግዘፍ በዘለለ መፍትሔውን ለመጠቆም ያነሡ ይሆናሉ፡፡ ግለኝነት ይስተዋልባቸዋል፡፡ ሀገራዊ ፋይዳቸውን ከመጠቆም ይልቅ የራስን የግል ስሜት ወይም ‹‹በርካቶች ሊቀበሉትና ሊከተሉት ይችላሉ›› ተብሎ የሚታሠበውን ነገር ይዞ የመጓዝ ነገር ይስተዋላል፡፡ በእርግጥ የተቃውሞው ጎራ ጥንካሬም ጥያቄ ውስጥ ገብቶ ማለት ነው፡፡ የህዝብን ድምጽ ለማስተጋባት የሚያስችል አቅም አለ ወይ? ሌላው ጥያቄ ይሆናል፡፡

ለ. ሁነኛ አማራጭ ስለመሆን

እንደኛ ባለው ሀገር የህዝቡን የፖለቲካ ዕውቀትና ብስለት ብሎም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች፤ ኢኮኖሚያዊ አቅምና፤ ከድሮ ጀምሮ ተያይዞ የመጣውን የፖለቲካ ልምድ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለህዝቡ ሁነኛ አማራጭ ነኝ ብሎ የሚቀርብ ፓርቲ ይዞ የሚመጣው አዲስ ነገር ምንጊዜም በህዝቡ ልብ ውስጥ ጥርጣሬ መፍጠሩ አይቀርም፡፡ እንዲህ ያለውን ነገር ደግሞ ከንጉሱ ዘመን አንስቶ አሁን እስካለንበት የኢህአዴግ ዘመን ድረስ ያለው ልምድ በህዝብ ዘንድ አመኔታን ወዲያው ለማግኘት አዳጋች እንዳደርገው አስባለሁ፡፡ በዚህ ረገድ በተለይ ምርጫ 97 እና በወቅቱ ሠፊ ተቀባይነት የነበረው ‹‹ቅንጅት›› ብሎም የምርጫው ውጤት በይፋ ከተገለጸ ወዲያ ያጋጠመውን ሁነት በፓርቲው አመራር አካባቢ የታየው የመፈረካከስ ዝንባሌ ከምርጫው አስቀድሞ ያልተሠሩ የቤት ሥራዎች ስለመኖራቸው በርካቶች እንዲያስቡ ምክንያት ሆኗል፡፡ ከጊዜ በኋላም በአመራር ላይ የነበሩት አካላት በጽሁፍና በቃል በተለያየ አጋጣሚ የሠጧቸው ሀሣቦች ክፍተቶች እንደነበሩ ያሣያሉ፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ራሳቸውን እንደአማራጭ ለማቅረብ ባሉበት ሁኔታ የውስጥ አሠራራቸውን በመፈተሸ አንዳች ለውጥ ለማምጣት መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህ እውነት በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ ዴሞክራሲያዊ ስለመሆናቸው የሀሳብ ልዩነቶች በተረጋጋና በሠከነ ሁኔታ ለመፍታት የሚሞክሩባቸውንና ለፓርቲ ዲሲፕሊን የሚያሳዩትን ተገዢነት ለህዝቡ የሚያሳዩባቸው መድረኮች ናቸው፡፡ በብዙ አጋጣሚዎች በምንመለከተው ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ ልዩነቶችን በሠላማዊ መንገድ ከመፍታት ይልቅ ሌላ ፓርቲ ማቋቋምና የግለሰቦችን ገመና ማውጣትና ‹‹ማራከስ›› ልማድ ሆኗል፡፡ በዚህ መንገድ ከላይ እንደጠቀስኩት ግልጽነት ያለው አሠራርና እውነትነትን የያዘ አስተዳደር መፍጠር ግድ ነው፡፡ ይህ ባይሆን ጥርጣሬን በህዝብ ልብ ከማጠንከር ባሻገር ጠቀሜታው አንዳችም እንኳ አይታየኝም፡፡

ሐ. በሥልጣን ላይ ያለውን መንግስት መቃወም

የሀገሬ ተቃዋሚዎች መቃወሙን ችለውታል ለማለት የሚደፍሩ እንደማይጠፉ አስባለሁ፡፡ ተቃውሟቸው እስከምን ድረስ ነው? የሚለው ነው ወቅታዊው ጥያቄ፡፡ ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የሚችል ተቃዋሚ ዕድሉን አንድ ደረጃ ከፍ ያደርጋል ብዬ አስባለሁ፡፡ በተቃራኒው በጣት ከሚቆጠሩት ፓርቲዎች (እነርሱም ቢሆኑ በርካታ ችግሮች ይነሱባቸዋል) ውጪ በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ለመቃወም ምርጫን የሚጠብቁትን ኢትዮጵያ ትቁጠራቸው፡፡

መ. አራተኛው ሚና

አራተኛውና አዲሱ ሚና በብዙ ረገድ ከእኛ የደረሰ አይመስለኝም፡፡ ገና ብዙ በርካታ ሥራዎች መሠራት አለባቸው፡፡ ከላይ የተጠቀሱትና ቀደም ሲልም በበርካቶች የሚጠቀሱቱ ሚናዎች ላይ መሠራትና የዴሞክራሲ ባህላችንም መዳበር ይኖርበታል ብዬ አምናለሁ፡፡

ውህደትን እንደአማራጭ

በርካታ ፖለቲከኞች በኢትዮጵያ ያሉ ፓርቲዎች ቁጥር ሲያሳስባቸው ይስተዋላል፡፡ ብዙዎችም የፓርቲዎቹ ፕሮግራም የተቀራረቡ እንደሆኑ በመግለጽ ተባብረው አልያም ተዋህደው ቢሠሩ ጠቃሚ እንደሆነ ይመክራሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ በዚህ ረገድ ያለውን እውነት ለመቀበል አሁን ያለው የፖለቲከኞች አስተሳሰብ ገና ነው ብለው የሚሞግቱም አሉ፡፡ 

አብርሃም ተስፋዬ


ቅዳሜ 30 ኦገስት 2014

‹‹ከመቃወም ባሻገር›› ፩

ሕገመንግስታዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በተለይም በአሁኑ ጊዜ የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡ እንዲህ ባለው ሥርዓት ደግሞ በቋሚነት (ሁልጊዜም) ሊታወስ የሚገባውና መዘንጋት የሌለበት በየትኛውም አጋጣሚ ሀገርን ወደፊት ለማራመድና ሀገርን እንደሀገር ለማስቀጠል የሚችል ሁነኛ አማራጭ የፖለቲከኞች ስብስብ (ፓርቲ) መኖሩ ነው፡፡ ይህ አማራጭ ደግሞ በደምሣሣው ‘ተቃዋሚ’ በመባል ይገለጻል፡፡ ምሁራንም እንደሚስማሙበት በበርካታ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቶች ተቃዋሚዎች ያነሠውን ስብስብ ወይንም የመንግስትነትን ሥልጣን ያልያዙቱ ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ እኒህ ተቃዋሚዎች ታዲያ መንግስት ራሱን እንዲፈትሽበት ምክንያት መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ በተለይ በዚህ ጉዳይ ላይ ጋናዊው ፖለቲከኛና ቀደም ሲልም የጋና የጤና ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት አልባን ባግቢን (Alban Bagbin) በዚህ ሀሳብ ይስማማሉ፡፡ እኚሁ ፖለቲከኛ የተቃዋሚዎችን ሚና አስመለክቶ በአራት ከፍለው ይመለከቱታል፡፡ የተቃዋሚዎች ሚና፡
ሀ. ‹‹ለድምጽ አልባዎች ድምጽ መሆን››
ተቃዋሚዎች በዋናነት መንግስት ሊተገበር ይገባዋል ተብሎ በህዝቡ የሚታመነውንና የሚያጉረመርምበትን ጉዳይ በማስተጋባት የመንግስትን ትኩረት እንዲያገኝ የማድረግ ሚና ይጫወታሉ፡፡ በዚህ አጋጣሚም የድምጽ አልባውን ህዝብ ድምጽ እንዲሰማ አንደበት ይሆኑለታል፡፡ ይህ ታዲያ ለመንግስትም ቢሆን ጠቀሜታው የትየለሌ ነው፡፡ የህዝቡን ስሜት ለማዳመጥ ያስችለዋል፡፡ የህዝቡን ፍላጎት ለመረዳት አማራጭ ነው፡፡ ይህ የተቃዋሚዎች ሚና ታዲያ የህዝቡን ልበሙሉነትና በራስ መተማመን ከማሳደግና ከማረጋገጥም ባሻገር ህዝቡ ስሜቱ፣ ፍላጎቱና እሳቤዎች በተገቢው መንገድ ለሚመለከተው አካል መቅረቡን ስለሚያስብ (ተግባራዊነቱ እንዳለ ሆኖ) ሀሣቡን በእነርሱ (በተቃዋሚዎች) በኩል ማድረሱን ራሱ እንደትልቅ ነገር ያየዋል፡፡
ለ. ‹‹ሁነኛ አማራጭ ሆኖ መቅረብ››
ቀደም ሲል ከላይ እንደገለጽኩት ሁሉ ህገመንግስታዊ ሥርዓትን በተገቢው መልኩ በሚተገብር ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ውስጥ ሀገርን እንደሀገር ወደፊት ለማስቀጠል የሚችል የፖለቲከኞች ስብስብ (ፓርቲ) ይኖራል፡፡ ስለሆነም የተቃዋሚ ፓርቲዎችም ታዲያ በዚህ አግባብ ሀገርን ለመምራት ራሳቸውን ሁነኛ አማራጭ አድርገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ በተገቢው አኳኸን የተቀየሠ መሪ ዕቅድ (ስትራቴጂ) ቀይሠው እንሟገትለታለን፤ ችግሩንም ለመፍታት ብሶቱን ወደመንግስት እናደርስለታለን የሚሉትን ህዝብ በእርግጥም ሊመሩት እንደሚችሉ አምኖና ተቀብሎ ከጎናቸው እንዲሠለፍ በአንድም ይሁን በሌላ አጋጣሚ ተገቢ ነው የሚሉትን የህዝቡን ችግር ለመቅረፍ የሚችሉ ፖሊሲዎችን ከመቅረጽ ይጀምራል፡፡ የህዝቡን ችግሮች ታዲያ ህዝቡ ድረስ ቀርቦ በማጥናት የህዝቡን ፍላጎት በማጤን በጥናት ላይ የተመሠረቱ ሊሆኑ ይገባቸዋል፡፡ በርካታ አለምአቀፍ የፖለቲካ ተንታኞችም እንደሚያስረዱት የህዝቡን ችግር ለመፍታት በስሚ ስሚ ከሚደርሱበትና በእልህ ከሚነዱት ይልቅ በሰከነ መንፈስ የህዝቡን ስሜት ጠልቆ ለመረዳት የሚያስችሉት በእርግጥም አማራጭ ለመሆን እንደሚችሉ ያስረዳሉ፡፡
ሐ. ‹‹በሥልጣን ላይ ያለውን መንግስት መቃወም››
ተቃዋሚ የሚለውን ስያሜ ከዚህኛው ሚና የመነጨ ስለመሆኑ ይነገራል፡፡ ይህኛው የተቃዋሚዎች ሚና በርካቶች የሚተገብሩትና እንደአንዳንድ ምሁራን አስተያየት አደናጋሪው ነው፡፡ ምክንያቱም ተቃዋሚዎች በሥልጣን ላይ ያለውን መንግስት የመቃወም ሚና አላቸው ሲባል፤ ‹‹ተቃውሞው እስከምን ድረስ ነው?›› የሚለው ጥያቄ ምላሽ ማግኘት አለበት፡፡ የትኛውም ህዝብ ጎድሎብኛል ለሚለው ነገር ምላሽ ለማግኘት ይሻል፡፡ በሀገሪቱ ያለውም መንግስት የህዝቡን ምላሽ ለመስጠት በቻለው መጠን ይተጋል (ተብሎ ይታሰባል)፡፡ ይህ የመንግስት ምላሽ የህዝቡን ጥያቄ በተገቢው መልኩ ካልመለሠ፤ ህዝቡ አማራጭ መፈለጉ ግድ ይሆናል፡፡
በእርግጥም ጥያቄውን የሚመልስለት የሚያዳምጠውና ሀገሪቱን እንደሀገር ለማስቀጠል የሚችል አማራጭ ሀይል መሻት፡፡ በዚህ የህዝብ መሻት ውስጥ ደግሞ የተቃዋሚዎች ሚና ሊሆን የሚገባው በሥልጣን ላይ ያለውን መንግስት መቃወም ነው፡፡ የመቃወም ‹‹ድንበር ልኬት›› በበርካቶች የተለያየ ርቀት ቢወሰድም ብዙዎች የተለያየ ትንታኔ ቢሠጡበትም የተቃዋሚዎች የመቃወም ዓላማ ጣሪያ ህዝቡን በማሳመን፤ የራሳቸውን ምርጥ (የሚሉትን) ፖሊሲዎች ለህዝቡ ግንዛቤ በማስጨበጥ በሥልጣን ላይ ያለውን መንግስት ህጸጾችን ለህዝቡ ከማሣወቅ ባሻገር ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ማሣወቅና በራሳቸው የፓርቲ አደረጃጀት ውስጥ በማስረጽ በህዝቡ ተቀባይነት እንዲኖራቸው ማድረግና ህዝቡ እንዲመርጣቸው ከፍተኛውን ሥራ መስራት ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ በምርጫ በሚያገኙት ስልጣንም ተጠቅመው ለህዝቡ ጠቃሚ ነው ያሉትን ፖሊሲዊች ማስፈጸም ይጠበቅባቸዋል፡፡
ይህም እውን እንዲሆን ተቃዋሚዎች  አለን የሚሉት ፖሊሲና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ከሀገርና ህዝብ ጥቅም አንጻር በሥልጣን ላይ ያለው መንግስት እየተገበርኩ ነው ከሚለው የተሻለ ስለመሆኑ በውስጥ አሠራራቸው የሚያሣዩት ዴሞክራሲ ብርቱ ማሣያ ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ በዚህም ተቃዋሚዎች በሥልጣን ላይ ያለው መንግስት ሊሸፍናቸው የሚፈልጋቸውንና በህዝብ ትኩረት እንዳያገኙ የሚያደርጋቸውን እውነታዎች ማጋለጥና አማራጭ የመፍትሔ ሀሳቦችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ሚና ህዝቡን በተለይም ከሙስናና ብልሹ አሠራር ለመታደግ ይጠቅማሉ፡፡
ይህንን በመተግበር ተቃዋሚዎች የመንግስትን ሥልጣንን ያለአግባብ መጠቀምን፣ ቢሮክራሲ፣ የሠብዓዊ መብት ጥሰትን፣ የህዝብ ሀብትና ገንዘብ ብክነትን እና ሌሎችንም የህዝብ ጥያቄዎች በማሳጣትና ሂስ በመስጠት ሀገራዊ ቁጥጥር ሥርዓት እንዲኖር ለማድረግ ይቻላቸዋል፡፡
መ. ‹‹አዲሡ የተቃዋሚዎች ሚና››
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይም በሉላዊነት (Globalization) ጋር በተያያዘ የመጣውን አለማቀፋዊ የሠብዓዊ መብቶች፣ የነጸነትና መልካም አስተዳደር ጽንሰሀሳቦች ጋር በተያያዘ የተቃዋሚዎችም ሚና አንድ ደረጃ አብሮ ከፍ ማለት አለበት የሚሉ አተያዮች ብቅ ብለዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም በሥልጣን ላይ ያሉ መንግስታት የሕግ የበላይነትን እና የሰብዓዊ መብትና ነጻነት መከበርን ማረጋገጥ በርክቶ የሚነሣባቸውና እንዲያረጋግጡ በተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶችና መንግስታት ጫናዎች ይበረክቱባቸዋል፡፡ ተቃዋሚዎችም ታዲያ ይህንን በመንግስት ላይ የተጣለ ኃላፊነት በምን ደረጃ ላይ እንዳለ የመከታተል ቦታና ጊዜ የመስጠትና በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ሥልጣን ላይ ካለው መንግስት ጋር በትብብር የመስራትና ሀገራዊ መግባባት እንዲኖር መስራት እንዳለባቸው ይታመናል፡፡
ይህ አዲሱ የተቃዋሚዎች ሚና በተለይም ለሠላም፣ ጸጥታና ዴሞክራሲ በጣም አደገኛ ሁኔታዎች ባሉባቸው ጊዜያት አብዝቶ ይጠበቃል፡፡ በሥልጣን ላይ ካለው መንግስት ጋር በምን ጉዳይ ላይ መግባባት ላይ መድረስ ተገቢ ነው የሚለውን ውሳኔ ማሳለፍ ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም ይህ ሁሉ በሚሆንበት ጊዜ ታዲያ ብሔራዊ (ሀገራዊ) እና ህዝባዊ ጥቅም በየትኛውም አጋጣሚ ለድርድር የሚቀርብ አይሆንም፡፡
የሀገሬ ተቃውሞ
በኢትዮጵያችን በርካታ የተቃውሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች አሉ፡፡ እኒህ ፓርቲዎች በተለያየ አጋጣሚ ብቅ ጥልቅ የሚሉትንም ይጨምራል፡፡ በቁጥር ከመበርከታቸውም በላይ በርካቶቹን የምናውቃቸው የምርጫ ሠሞን ነው፡፡ ምንም እንኳ አንዳንድ ብርቱ የሚባሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቢኖሩም የምርጫ ወቅት ላይ ራሳቸውን ዕጩ በማድረግ ብቻ አሸናፊነት የሚናፍቁ በርካቶች ናቸው፡፡ ከላይ ያስቀመጥኳቸውን የተቃዋሚዎች ሚና እንደመስፈርት ወስደን እንለካቸው ብንል ምን ያህሉ ይሆኑ በእርግጥም የተቃውሞውን ጎራ በተገቢው መልኩ ከህዝቡ ፍጆታ እያዋሉት ያሉት? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡ ምናልባት አንድ በአንድ ብናየው መልካም ይመስለኛል፡፡

(ይቀጥላል)

ዓርብ 13 ጁን 2014

አደባባዩን ፍለጋ


የግብጹን ታህሪር አደባባይ አልረሳውም፡፡ በፍጹም የበላይነት፤ ህዝብ ተቆጣጥሮት እንደነበር አውቃለሁና፡፡ የቱኒዚያውን የህዝብ ማዕበል ያስተናገዱ ጎዳናዎችንም አልረሳቸውም፡፡ ሊቢያውያንም የተዋደቁባቸውን ጎዳናዎች ለመርሳት ይከብደኛል፡፡ የእነዚህንም ሀገራት መሪዎች ብረሳ ዋጋ አይኖረኝም፡፡ እንዴት ይረሳሉ? በፍጹም፡፡

ቦአዚዝ የሚባልንም ወጣት አልረሳውም፡፡ ለዛውም ቱኒዚያዊ ወጣት፡፡ ኑሮን ለማሸነፍ የከፈለውን ዋጋ ብረሳ ነፍሱ ትቀየመኛለች፡፡ እንዲህም ላለው ጀግና፤ መረሳት ክብር አለመስጠት ነው፡፡ በወጣትነት ዕድሜው ለሀገሩ (ባያየውም) ታላቅ ግብር የከወነ የለውጥ አባትና አምባሳደር ነው፡፡ ተጨቆንን ያሉ ሁሉ የተከተሉት የእርሱን ቁጣ ነበር፡፡ በእራሱ ላይ የወሰደው እርምጃ በጣም ከባድ የሚባል ውሳኔ ነው፡፡ እዚህኛው ስሜት ላይ ለመድረስ የሚያስችለው ስሜት የትኛው ይሆን? (በቅርቡ በእራሱ እጅ ያለፈው ወዳጄን አስታወስኩ፡፡ ከማለፉ ከጥቂት ቀናት በፊት ወደቤት እየገባሁ ሳለሁ አግኝቼው ያጫወተኝ ሁሉ ከልቤ አለ፡፡ ማለፉን ስሰማ ማመን አቅቶኝ ነበር፡፡ እርሱ ሲቀር ሁሉም ነገር አብሮ ቀረ፡፡ ቴዲ (ገጀራው) ነፍስህን ይማረው፡፡ ከርዕሴ እንዳልወጣ ወደዋናው ጉዳዬ ልመለስ፡፡)

ባህሬይን፣ የመን፣ ሊቢያና ሌሎችም የአረብ ሀገራት ከጥቂት አመታት በፊት በህዝብ ተቃውሞ ማዕበል ተመትተው ነበር፡፡ ዜጎች አደባባዮችን (ገላጣና በጣም የተንጣለሉ) ‹ምሽግ› አድርገው ከርመውባቸዋል፡፡ ይህ ኹነት ታዲያ በቀጥታ በተለያዩ መገናኛ ብዙኸን ለአለም ህዝብ ሲደርስ ሰንብቷል፡፡ አስደናቂ ጊዜያት አልፈዋል፡፡ በእነዚህ ጊዜያት በእኛም ሀገር ኢትዮጵያ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ዜጎች የየዕለቱን ሁኔታ በተለያዩ ድረገጾች ይከታተሉ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡

አደባባይ ላይ ውሎ የማደርን ጥበብ ለአረብ የሠጠው ማነው; ብለን ጠይቀንም ነበር በወቅቱ፡፡ ታዲያ በርካቶች ማለትይቻላል በአንድም ይሁን በሌላ ጊዜ በርካታ የደም ዋጋ ተከፍሎበት ለውጥ ሆነ፡፡ በግብጽ የነበረው ደግሞ በተለይ ወታደሩ አካባቢ የታየው ገለልተኝነት አስደናቂ ተብሎ ነበር፡፡ (ከልብ ይሁን አይሁን አስካሁን ግልጽ አይደለም፡፡ ምክንያቱንም ወታደራዊው ቡድን ስልጣን ከያዘ ወዲያ በጣም ጨከን ያሉ እርምጃዎችን ታዝበናልና ነው፡፡) በጊዜ ሂደት አላስፈላጊ ነገሮች መሆናቸው ቢታመንም፡፡ አሁንም ድረስ የሚታዩት ነገሮች አንዳንድ ጊዜ በጥልቀት መታየት እንዳለባቸው ያመላክታል፡፡ አሁንም ድረስ በወታደራዊው ክንፍ ያለው ሁኔታ ድጋፎች እንዳሉት ሁሉ ቅዋሜም እንዳላጣ እየተመለከትን ነውና፡፡

አደባባይ የወጡት ዜጎች አደባባይ ውለው፤ አደባባይ አድረው ለውጥ አመጡ፡፡ (አደባባይ ስለነበራቸው፡፡) በዚህ ሁሉ ውስጥ ታዲያ የሆነው ሆኖ ዛሬ ላይ ብንሆንም የለውጥ ማደሪያው የት እንደሆነ በብርቱ መልዕክት አስተላልፎ ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡ በተለይ ቀደም ሲል በሀገራችን ኢትዮጵያ 1997 ላይ የሆነውን ሁነት ለሚያስታውስ ሰው ደግሞ የአደባባይ ትርጉሙ በእርግጥም ይገባዋል ለማለት ይቻላል፡፡ መቼም ያንን አመት መናፈቅ ሀጥያት እንደማይሆን አስባለሁ፡፡ ‹ነጻ› ‹ፍትሐዊ› እና ‹ዴሞክራሲያዊ› ሂደት የነበረው ምርጫ ለማካሄድ በሚል የተደረገው ሁሉ ግሩም ነበር፡፡ አድባባዩም በወቅቱ ክፍት ነበር፡፡
ወደቀደመውም ዘመን እንመለስ ካልን ተማሪዎችም ሆኑ ዜጎች ሠልፍ ለማካሄድ በፈለጉ ወቅት አደባባዩን መፈለጋቸው ግልጽ ነበር፡፡ የቀድሞ ተማሪዎች ንቅናቄን በተለያየ ወቅት የተጠቀሰ ጉዳይ ስለሆነ መመለስ አይሁንብኝ፡፡ ታሪክ በእራሱ መንገድ ያስተናግደዋልና፡፡

ይህንን ሁሉ ማለቴ ታዲያ ያለነገር አልነበረም፡፡ ቅዳሜ ግንቦት 16 ቀን 2006 ዓ.ም. በመድረክ ፓርቲ መሪነት የተጠራውንና፤ የተካሄደውን ሠልፍ ተመልክቼ ነበር፡፡ ከመነሻው ሠልፉን አልተመለከትኩትም ነበርና ሠልፉ የሚካሄድበትን ቦታ ለማጣራት ወዳጆቼን ጠየቅኩ፡፡ ቦታውን ነገሩኝ፡፡ አካባቢውን ቀደም ሲልም ስለማውቀው፤ ሰፈሩ አልጠፋኝም፡፡ ‹አደባባዩን› ግን አላውቀውም፡፡ ስለሆነም አንድ መላ ዘየድኩ፡፡ ጠንከር ያለውን የአካባቢውን ጥበቃ አየሁኝ፡፡ ግራ ቀኙን መመልከት ጀመርኩ፡፡ በሁለቱም በኩል ያሉትን የጸጥታ ኃይሎች ይዤ ብሄድ እንደምደርስ አሰብኩ፡፡ ‹አደባባዩን› ፍለጋ ላይ ነኝ፡፡ ጉዞዬ አላበቃም፡፡ በመንገዴ ሁሉ ‹አደባባይ› እናፍቃለሁ፡፡  ከቦታው ደርሼም ታዘብኩኝ፡፡

የሠልፉ ተሳታፊዎች ከመድረኩ የሚነገረውን እየተቀበሉ ያስተጋባሉ፡፡ ዞር ዞር ብዬ ለመቃኘት ሞከርኩ፡፡ በተቻለኝ አቅም ዙሪያዬን ለማየት ችያለሁ፡፡ ሁሉም ዞሮ የሚመለከተውን ይመለከታል፡፡ የፍርኃት ድባቡ ከባድ ነበር፡፡ ሁሉም ሰው ያያል፡፡ ጥርጣሬው ሌላ ነበር፡፡ እኔ የማስበው አደባባይ ሌላ ነበር፡፡

የተሳታፊዎቹን ሁኔታ ለተመለከተ፤ እውነት ለመናገር አስገራሚ ነበር፡፡ ከልባቸው ሆነው ሁኔታውን በብርቱ የሚሳተፉ ነበሩ አንዳንድ ደግሞ ሰዎችንና የግለሰቦችን እንቅስቃሴ በትኩረት ሲከታተሉ የነበሩ እንደነበሩም ታዝቤያለሁ፡፡ ሞባይላቸውን አውጥተው ሁኔታውን የሚቀርጹ ምስል የሚያስቀሩ እንደነበሩ ሁሉ ሞባይል ወይም ሌላ መሰል ነገር ወደአፋቸው አስጠግተው በጣቶቻቸው መሀል የምስል መመልከቻና ማቅረቢያ (ሌንስ) ብቻ እያሳዩ የጎሪጥ ሁነቱን የሚመለከቱ ነበሩ፡፡ እነዚህኞቹ ምናልባት ምስል እያስቀሩ እንደሆነ ገመትኩ፡፡

የሰልፉ አስተባባሪዎች ህዝቡን ‹በጨዋ ደንብ› ይሉታል ደጋግመው፡፡ ይሄ የ‹ጨዋ ደንብ› ምንድነው? በቦታው የነበሩ ወዳጆቼን ጠየቅኩኝ፡፡ እነርሱም ከመጀመሪያው ጀምሮ የነበረውን ጨምረው ነገሩኝ፡፡ የተጻፉ መፈክሮችን ሳይቀር የእኛን ተጠቀሙ ይሉ ነበር፡፡ በሠልፉም መካከል አንዳንዶች መፈክር ሊያሰሙ ሲሉ የ‘እኛን ብቻ ቆይ’  ይሉ እንደነበርም ጭምር፡፡ ይህ እንግዲህ ከምን እንደመነጨ መገመት ከባድ አይደለም፡፡ (የዚህች ጽሁፍ አቅራቢ ታዲያ የሰልፉን አስተባባሪዎች አልያም ፓርቲውን እየተቸ አለመሆኑን ልብ ይባልልኝ፡፡) የፍርሃት ቀንበር ተጭኖብን፤ እንዴት ነው ጥያቄዎቻችንን በተገቢው ሁኔታ ለማቅረብ የሚቻለው?

ፈቃድ ተጠይቆበት፤ በቂ የጥበቃ ኃይል ተመድቦለት፤ ህጋዊ ዕውቅና ያለውን አንድ ሰልፍ ለማካሄድ፤ ህጋዊነቱን በጠበቀ ሁኔታ ማንኛውንም ጥያቄ ይዞ ቢነሳ ምን ችግር አለው? የሰልፉስ ታዳሚ የተሰማውን ቢገልጽ ምን ክፋት አለው? በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞና ጥያቄውን የሚያሰማ ህዝብ ፈር ባልለቀቀ ሁኔታ በተገቢው መልኩ ጥያቄውን ቢጠይቅ ምን ችግር ይኖነው ይሆን? እንዲህስ ያለው ስጋት እስከመቼ አብሮን ይቆይ ይሆን?

በቦታው ከነበሩት ተናጋሪዎች መካከል አንደኛው፤ ለሠልፉ የጥሪ መልዕክት ሲያስተላልፉ የነበሩና ቅስቀሳ ላይ የነበሩ አስተባባሪዎች መታሰራቸውን ተናግረው ነበር፡፡ እንዲህ ባለው ወቅት ላይ እነዚህ ግለሰቦች የታሰሩት ለም ይሆን; ተገቢ ያልሆነ ድርጊት ፈጽመው ከሆነም መንግስት እንደመንግስት ስለምን ቀድሞ ለህዝቡ አያሳውቅም? ይህንን የምጠይቀው ሰልፎችና ተቃውሞዎች ብዙ ጊዜ በእስር መታጀባቸው ስለሚያስገርመኝ ነው፡፡ ሰልፍ ካለ እስር አለ አይነት ነገር ይስተዋላል ብዙ ጊዜ፡፡ መንግስትስ ዜጎችን በማሰር የሚያተርፈው ስንት ይሆን?

ወደ አደባባዩ ልመለስ፡፡ ሠልፉ እየተካሄደ ያነበረበት ቦታ ላይ ብሆንም፤ በሀሳብ ነጎድኩ፡፡ ጉዞ ወደ1997፡፡ መለስ ብዬ ደግሞ ወደውስጥ አልፌ ያለሁበትን ቦታ አየሁና፤ አደባባዩን መፈለግ ጀመርኩ፡፡ አደባባዩስ? አነስተኛ በምትባለው ሜዳ ላይ ነው ያለሁት፡፡ ዳር ቆመው የሚታዘቡትን ጨምሮ ሌሎችም ንግግር ከሚያደርጉት የመድረክ አመራሮችና አባላት የሚባለውን ያዳምጣሉ፡፡ በቅርቡም በተከታታይ ሠልፎቹ የተካሄዱት እዚሁ እንደሆነ ገመትኩ፡፡ አካባቢው ሲጠራ ሰምቼያለሁ፡፡ ስለሆነም ሠልፍ መካሄዱን አወቅኩኝ፡፡

እኔ ግን በቦታው ሆኜ ባላውቀውም ታህሪር ላይ የነበረውን ጀብድ አሰብኩት፡፡ 1997 ላይ ራሴን አስቀምጬ መስቀል አደባባይን ናፈቅኩት፡፡ ያንን የህዝብ ማዕበል በእዝነ ህሊናዬ ተመኘሁት፡፡ ዳግም ምልሰት ወዳለሁበት ሆነ፡፡ በዚህ ሜዳ የተካሄዱትን ሰልፎች እንደው ዝም ብዬ ማሰብ ጀመርኩ፡፡እንዲህ ባሉ ሁኔታዎች የተከወኑ እንደሚሆኑ አስቤ፤ ሀሳብም፤ ድንጋጤም ሀዘንም ወረረኝ፡፡ የአደባባይ ናፍቆት ሆነብኝ፡፡ እኔም አደባባይ ብሆን ተመኘሁ፡፡ ስጋት ባረበበት ምድር ላይ ለካንስ አደባባይም ይጠፋል? ስለሰልፉ ማሰብ ስጀምር ፍርኃታችን የት እንደደረሰ በማሰብ እሳቀቃለሁ፡፡ ሀሳባችንን ለመግለጽ ምንና እንዴት ማድረግ እንዳለብን ማሰብ የጀመርን ‘ለት አንዳች ስህተት እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ማንም በማንም ሀሳብ ላይ ቁጥጥር ለማድረግ የሚቻለው ቢኖር፤ እርሱ የተሳሳተ ነውና፡፡ ማሰብ፤ ያሰብነውን መግለጽም ሁሉ የእኛ የሰው ልጆች ጸጋ ስለሆነ፡፡ ለዚሁም የሚሆኑ፤ ገላጣ ምሽጎች (አደባባዮች) ያስፈልጉናል፡፡

አደባባዮች ጌጦች ናቸው፡፡ አደባባዮች ህዝብ ያለውን ብሶት የሚያሳይባቸውና ያሳየባቸው ገላጣ ምሽጎች ናቸው፡፡ ሀገሬም ታዲያ ይህንን መሰሉን አደባባይ ናፈቅኩት፡፡ ህዝብ በይፋ ያለምንም መሳቀቅ ወጥቶ ሀሳቡን የሚገልጽበት ግልጽ ምሽግ፡፡ የእኛነታችንን ጥያቄዎች በግልጽ የምናሰፍርባቸው፤ ልዩነቶቻችን ላይ የምንማከርባቸው፤ የእኛ ምሽጎች፡፡


ከዚህም ወዲያ ሠልፎች እንደሚኖሩ አስባለሁ፡፡ ታዲያ የትኛው አደባባይ በግልጽ ሊያተያየን ይችል ይሆን? ስለሆነም አደባባዩን ፍለጋ ላይ ያለን ይመስለኛል፡፡ ገላጣውን፤ በስርዓት ያለመሸማቀቅ ሆ ብለን ድምጻችንን የምናሰማበት፡፡ ከፍርሃት ተላቀን በቀና መንፈስ ተረዳድተን የምንከራከርበት፤ የምንነጋገርበት፤ ሀሳብ የምንለዋወጥበት፤ ለውጥ የምንጠይቅበት፤ ለውጥ የምናመጣበትም አደባባይ፡፡ ሠልፉ እየተካሄደ ነው፡፡ እኔ ግን አደባባዩን ፍለጋ ላይ ነበርኩ፡፡ አሁንም ፍለጋ፡፡ አደባባዩን፡፡ 

አብርሃም ተስፋዬ

ሰኞ 12 ሜይ 2014

የተከበሩ የአቶ ግርማ ሠይፉ ተቃርኖ


ሰሞነኛው ወሬ የአዲስ አበባ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ነው፡፡ አዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙት የፊንፊኔ ልዩ ዞኖችን ባማከለ መልኩ ተሰናዳ የተባለው ማስተር ፕላን በርከት ያለ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ በተለይ በዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆች እና በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ነዋሪዎች ሁኔታውን በጣም አክርረው ተቃውመውታል፡፡ በዚሁም መነሻ አሳሳቢ የሚባል አይነት ተቃውሞና ግጭት ተከስቶ የሰው ህይወትና የንብረት ውድመቶችን እንዳስከፈለ ሰምተናል፡፡ በተለይ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ ሁኔታውን ከቦታው የሚዘግቡት ስለነበሩ በምስል የተደገፉት መረጃዎች ልብ ይሰብሩ ነበር፡፡ በተለይ የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉት ዜጎች ላይ የተፈጸመው ግድያና የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎችን ጉዳይ አስመልክቶ መንግስት አንዳች ነገር መከወን አለበት፡፡ እንዲሁ ዝም ብሎ ሊታለፍ የሚገባው አይደለም፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም ታዲያ ይመለከተናል ያገባናል ያሉና የሚሉ ግለሰቦች ኃሳባቸውን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ኃሳባቸውን መስጠት መብታቸው መሆኑን አምናለሁ፡፡ ህገመንግስታዊ መብታቸውም ጭምር እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ስለሆነም፤ ኃሳባቸው አከብራለሁ፡፡ በተለይ ደግሞ አንዳንድ በሀገሪቱ የሥልጣን እርከን ቁንጮ ከሆኑት አካባቢ ያሉትን ግለሰቦች ኃሳብ በብርቱ ማክበሬን ሳልጠቅስ ባልፍ ደስ አይለኝም፡፡ ስለሆነም ሙግቴ ሀሳባቸውን ብቻ ስለመሆኑ አስምሬ እናገራለሁ፡፡ አዋጅ! አዋጅ! አዋጅ! ሙግቴ ከኃሳባችሁ ብቻ ነው፡፡ እነሆ ለመጀመር ፈቃድ ሆነ፡፡

የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ ማሩ ግንቦት 2 ቀን 2006 ዓ.ም. በወጣችው ፋክት መጽሔት ቅጽ 2 ቁ. 45 ላይ ያሰፈሩትን ሀሳብ አነበብኩኝ፡፡ ጉዳዩ ግራ ስላጋባኝ ደግሜ አነበብኩት፡፡ የተከበሩት የምክር ቤት አባል በአንድ ወቅት ጢስ አባይን ለማየት በሄዱበት ወቅት ካደረጉት ውይይት ጋር አስታከው በወቅቱ የነበረውን የ‹‹ቦታ››ውን ጎጃሜነትና ጎንደሬነት አንስተው ከተነጋገሩ ወዲያ ከወዳጃቸው ይልቅ፤ የአካባቢው እረኛ የተሻለ መረዳት እንዳለው ገልጸው ነው የሚጀምሩት፡፡ እረኛውን ቦታው ምዕራብ ጎጃም በመባሉ የተሰማውን ሲጠይቁት፤ ‹‹....ውሃውም መሬቱም እዚሁ ድሮ ያለበት አይደለ?›› ብሎ እንደጠየቃቸውና የዕድሜ ልክ ትምህርት እንደሰጣቸው ገልጸዋል፡፡ ከእረኛ ለመማር ዝግጁ ለሆነ ሰው ሊማር እንደሚችል ነግረውናል፡፡ ግን ለጥያቄያቸው የተሰጣቸው መልስ ምናልባት አሁንም ድረስ በደንብ ያልተገለጠላቸው ከሆነ ምላሽ መስጠት ተገቢ መሰለኝ፡፡ ምናልባት እረኛውን ባልሆንም፤ የእርሱ አረዳድ እርሳቸው ካነሱት ጭብጥ ጋር ፈጽሞ የገጠመ ስላልመሰለኝ ነው ይህንን ማለቴ፡፡

እረኛው አለ ያሉት ‹‹....ውሃውም መሬቱም እዚሁ ድሮ ያለበት አይደለ?›› ነው፡፡ ውሃና መሬትማ የት ይሄዳል? ሂያጁ ሰው ነው፡፡ ድሃው ገበሬ፡፡ ይህ ድፍን ኢትዮጵያን ከሚቀልቡት በርካታ ገበሬዎች ተርታ የሚሰለፈው ድሃው የእናት አለም ኢትዮጵያ ገበሬ ነው፡፡ እረኛውም መልሱን ሲሰጥ ሊሰጥ የሚችለውና የቻለው በዛን ወቅት የነበረውን እውነት ተገን አድርጎ እንጂ አሁን አሁን በተለይ ከልማት ጋር በተያያዘ የመንግስትን የመሬት ፍላጎት ለመሙላት ሲባል ከ‹‹መሬታቸው›› ላይ የሚፈናቀሉትን ሰዎች ስሜት ያገናዘበ ባለመሆኑ ክቡር አቶ ግርማ ‹‹ክፉኛ›› ተሳስተዋል፡፡ ጋራ ሸንተረሩማ የት ይሄዳል፡፡ ያው የኢትዮጵያ ነው፡፡

እኑህ ገበሬዎችም ሆኑ፤ በየዩኒቨርሲቲው የሚገኙት ልጆቻቸው ታዲያ እንደው ልማትን በመጥላትና በመጠየፍ ተቃውመውታል ብዬ ለማሰብ ይከብደኛል፡፡ ልማትማ የሚጠላ አንዳችም እንዳለ እጠራጠራለሁ፡፡ የህዝቡ ጥያቄ የልማቱ ተካፋይ የመሆን መስሎም ይታየኛል፡፡ እንዲህ ያሉት ጥያቄዎች ደግሞ በአንድም ይሁን በሌላ አጋጣሚ ገበሬዎቹ እራሳቸውና ዘመዶቻቸው፤ ብሎም በሌላ አካባቢ የሚገኙ ዜጎች ላይ ከደረሰውና ከሚደርሰው በመነሳት የሚመነጭ ጥያቄ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ህዝብ እንደ ህዝብ በይፋ ልማትና ለመጥላት የሚያስችል አንዳችስ ምክንያቱ እርሱ ምን ይሆን?

ክቡርነትዎ፤ አሁን በየዩኒቨርሲቲው የሚገኙት ተማሪዎች የኢህአዴግ ትውልዶች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ጎጠኝነትን በሚያሞግስ አጠቃላይ የፖሊሲ አቅጣጫ እየተመሩ የመጡ ናቸው ብለው ደምድመዋል፡፡ የኢህአዴግ ፖሊሲም ይሁን የማን አሁን ባለው ሁኔታ ብሄርን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ተዋናይ መሆን ግድ የሆነ ጉዳይ ይመስለኛል፡፡ በመሠረቱም እኔ በግሌ የብሔር ጉዳይ ተፈጥሯዊ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ማንም ቢሆን ስለማንነቱና እርሱ ከየትኛው ግንድ እንደሆነ ለመጠየቅ ገና ስለuuና ስለuu ነገዶች ሲማር መመርመር እንደሚጀምር እገምታለሁ፡፡ ኩሽ፤ ሴሜቲክ፤ እየተባለ ሲማር ከየት ነኝ ብሎ መጠየቁ ሰዋዊ ነው፡፡ ከዚያም ወዲህ ባለው ጉዳይ የኢትዮጵያን ታሪክ ፍጹማዊነት አበክረው ካላመኑ በቀር በደል ደርሶብኛል የሚል የትኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ፤ በአንድ አጋጣሚ ተነስቶ እኔ ለምን እንዲህ እንዲፈጸምብኝ ሆነ ብሎ በጠየቀ ቁጥር ጎጠኛ እየተባለ የሚፈረጅ ከሆነ፤ ጎጠኛ የሚሉትም አካላት በእራሳቸው አግባብ መጠየቅ ያለባቸው ይመስለኛልና ነው ይህንን ማለቴ፡፡ የኢትዮጵያ አንድነት ሊጠናከር የሚችለው ሌሎችን በመደፍጠጥ ነው ብዬ ስለማላስብ ነው ይህንን ማለቴ፡፡

ጎጥም፤ ጎሳም፤ ብሔርም፤ ምንም ሊባል ይችል ይሆናል፡፡ ሁሉም ግን ተፈጥሮ ለሰው ልጅ የቸረችው ነው፡፡ ወደእራሱ በቀረበ ቁጥር የሚታወቀው፤ አንዳች የማንነት ቁስል ነው ይሄ፡፡ ስለሆነም፤ ጥያቄ መነሳቱ ስህተት ነው ብዬ አላስብም፡፡

ባይሆን፤ የእርስዎ ትንታኔ ጥያቄውን ምናልባት በትክክል ካለመረዳት የመነጨ ሊሆን ይችላል፡፡ በእርግጥ ከማስተር ፕላኑ ጋር በተያያዘ የሚነሱት ሀሳቦች ከበርካታ ጽሁፎች ላይ ለመረዳት እንደቻልኩት፤ እንዲሁም ከድረ-ገጾች ላይ ባገኘሁት መረጃ መሰረት፤ (ሌሎቹ ጥያቄዎች እንዳሉ ሆነው እርስዎ ባነሱት የማስተር ፕላኑ ጉዳይ ላይ ብቻ አተኩራለሁ) ኢትዮጵያችን የጋራ አይደለችም ከሚል የመነጨ አይደለም፡፡ እንዲህም ነው ብዬ አላስብም፡፡ መነሻው የህዝብ ጥቅም ይመስለኛል፡፡ ህዝቡ ደግሞ ይጠቅመዋል ብሎ እዚህ ሆኖ መደምደም በእኔና በእርስዎ አያምርም፡፡ ምክንያቱም እዛው ያሉ፤ በዚህ ሁነት ውስጥ የሚኖሩት ዜጎች በጉዳዩ ላይ ያላቸውን ሃሳብ በግልጽ ማስተጋባት የሚችሉበት ሁነት መኖር ነበረበት፡፡ እርስዎም እንደሌሎቹ ሁሉ (በጉዳዩ ላይ የኮሚቴ አባል ናቸው ተብለው በብሔራዊው የቴሌቪዥን ጣቢያ የቀረቡ ባለሥልጣናት) አሁን ያለው ዓለም አቀፍ ልምድ የሚያሳየው ይህንን እንደሆነና በጋራ የመልማት ስትራቴጂም የግድ መሆኑን አንስተው ሞግተዋል፡፡ ሙግትዎ አለማቀፋዊውን ልምድ በተመለከተ ጥሩ ሊሆን ይችል ይሆናል፡፡ ሀገራዊውም ልምድ ታዲያ በእርግጥም ከታሰበበት መወሰዱ ግድ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ከልማት ጋር በተያያዘ ከመኖሪያቸውና ከቀዬያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች አሁን እየከፈሉ ያሉትን ዋጋ እነርሱን ሆኖ ማሰብ ያሻል፡፡ እኛ ምናልባት ሞልቶልን ቢሆንም ቅሉ፤ የእነዚህ ዜጎች መፈናቀል የወር ቀለባችንን እንዴት ብለን ከወደየት ልንሸምት እንደምንችል አያስጠይቀን ይሆን? ነገን ማን ያውቃል? አለማ አቀፋዊውም ልምድ ታዲያ በርካታ ጥያቄዎች መመለስ አለበት፤ የተገበሩት እነማን ናቸው? ሲተገበርስ እንዴት ነው የተተገበረው? እንዲህስ ያለው ታላቅ ዕቅድ እንዴትና ከየት ነው መመንጨት ያለበት? ማንስ ነው በማን ላይ መወሰን ያለበት?... እኒህና ሌሎችም መሰል ጥያቄዎች መመለስ ያለባቸው ይመስለኛል፡፡

ዘመናዊው የሥራ አመራር ሂደት በተለይም አሁን ወደተሳትፎአዊው ምልከታ ያመዝናል፡፡ ይህን ምልከታ በርካታ የሙያው ታላላቅ ምሁራን መስክረውለታል፡፡ ይህንን ጉዳይ ማንሳቴ ዝም ብሎ አይደለም፡፡ ህዝብ በእራሱ ላይ ሊወሰንበት፤ ሊተገበርበት ያለውን ነገር ማወቅ አለበት፡፡ ከማንም በላይ ቀድሞ ማወቁ ግድ ነው፡፡ ይህንን ማወቅና ማሳወቅ ደግሞ የመንግስት ድርሻ ነው፡፡ ውይይትም ሲደረግ ደግሞ ከባለስልጣናቱ ጋር ብቻ ሳይሆን ታች ወርዶ ከህዝቡ ነው መጀመር ያለበት፡፡ ወደድንም ጠላንም፤ ህዝብ ያልፈቀደው ነገር ተግባራዊነቱ ባያጠራጥር እን£ ቅቡልነቱ ጥያቄ ውስጥ ስለሚገባ አደገኛነቱ አብሮን ይዘልቃል፡፡ ስለሆነም ቆም ብሎ ማሰብ ግድ ነው፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ እርስዎ አባል የሆኑበት ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ለአሜረካ ድምጽ ራዲዮ በሰጡት ቃለመጠይቅ በተወሰነ ደረጃ ስህተቱን ማመናቸው (ሌሎች የሚነሱ ጥያቄዎች እንዳሉ ሆነው) ከመሪ የሚጠበቅ ማጽናኛ ቢሆንም፤ አሁንም ወደላ መለስ ብሎ ማሰብ እንደሚገባ ባለዎት አጋጣሚዎች ሁሉ ቢነግሩ፤ ብሎም ቢመክሩ ተገቢ ይመስለኛል፡፡

ጥያቄው ግን በቀና መንፈስ ለተመለከተው ተገቢ ይመስለኛል፡፡ በቦታው ያሉት ገበሬዎች መፈናቀል በእርግጥም ያሳስባል፡፡ ገበሬዎቹን ብቻ አይደለም፡፡ አዲስ አበባ ላይ ለመኖር ተፈትኖ ሲያበቃ ጥግ ፍለጋ ወጣ ያለውም ህዝብ ቢሆን፤ በልማት ሰበብ መገፋቱ የማይቀር ይመስለኛል፡፡ እንዲህ ባለው ጊዜ ውስጥ ደግሞ ከማንም በላይ ህመሙ ከእነዚህ ዜጎች በላይ ሊሰማው የሚችል ይኖር ይሆን? ወላጆቻቸው በመፈናቀል uፍ ላይ ያሉ ተማሪዎችስ እንዴት ዝም ብለው ሊማሩ ይችላሉ? የሆነው ሆኖ፤ አሁን ያለው ነገር መርገቡ ጥሩ ነው፡፡ ቢሆንም ግን ለወደፊቱ የምናስቀረው ቂም እንዳይኖር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍታት ያለብን ጉዳይ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡


አክባሪዎ አብርሃም ተስፋዬ

እሑድ 13 ኤፕሪል 2014

የደብተራው አምሳሉ ጡዘት!!!

http://www.goolgule.com/my-reply/ ሠዓሊ (ደብተራ) አምሳሉ ገ/ኪዳን ለቀደመው ጽሁፉ አስተያየቶች የሠጠውን ምላሽ በመንተራስ የተጻፈ፡፡

ለምላሽህ ምላሽ ቢሆን

ደብተራው አምሳሉ የቅድመ አያቶቹን ታሪክ ይዞ ፉከራና ቀረርቶውን ያስነካዋል፡፡ ነጻነትህ ጥሩ ሆኖ ሳለ፤ ደብተራነትህ ሳይጎዳህ የቀረ አልመሰለኝም፡፡ ግድ የለህም ጎድቶሃል፡፡ ምላሽ ይሁናችሁ ብለህ የደገምከው የመሰል አያቶችህን ተረት ነው፡፡ የዛን ዘመን ተረት ደግሞ ታሪክ እንዲሆን ትወዳለህ፡፡ በሌላ ወገን ያለውን ለማመን ግን አሻፈረኝ ባይነትህ ገርሞኛል፡፡ በመሠረቱ የወደዱትን ጽፈው ታሪክ አስብለው ያለፉት ያንተው ነገስታት እነሆ ዛሬ ላይ ታሪክ አልባ ሀገር ብትኖረን ተጠያቂ እንደሚሆኑ አስባለሁ፡፡ የእራሳቸውን ማንነት ለማግዘፍ ሲሉ፤ ቅራቅንቦዋቸውን ሁሉ በመዝገብ ሲያኖሩ ከርመው፤ አንዳች እውነት ፍለጋ ምን ያህል እያደከሙን እንዳሉ ሳስብ አዝናለሁ፡፡ ነገስታቱ በረባ ባልረባው ሁሉ የእነርሱን ጀብድና መልካምነት አስፍረው አልፈዋል፡፡ አንዳንዴም ሳስበው በንግስናቸው ወራት ጦርነት ባልነበረበት ሁሉ ጀብድ ያስመዘገቡ ይመስለኛል፡፡ ገራሚ ናቸው ብቻ፡፡ እነርሱን በመሀከሉም ማንሳቴ ስለማይቀር ወዳንተ ልመለስ፡፡

በ‹‹እነሆ ምላሻችሁ›› ጽሁፍህ ለማንሳት የሞከርካቸው ሀሳቦች በዋናነት ለአንድ ግለሰብ ጽሁፍ ላይ የተንተራሰ ቢሆንም፤ ለሁላችሁም መልስ ይሆናል በማለትህ አንብቤዋለሁ፡፡ ነገር ግን አሁንም ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ሀሳብህ የኦሮሞን ህዝብ ኢትየጵያዊነት ለመጠራጠርህ በድጋሚ ከማረጋገጥ የዘለለ አልሆንልህ ቢለኝ ደጋግሜ አነበብኩት፡፡ ሀሳብህን በእርግጠኝነት ስሜት ስታነሳ ጥንቃቄ የሚጎድልህ መሰለኝ፡፡ አንብበህ ያወቅከውን ነገር ከነማስረጃው ብትናገረው መልካም የሚሆን ይመስለኛል፡፡ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ነው ካልክም በዛው መልክ ብናውቀው ጥሩ ነበር፡፡ አንተ ግን ከወቅቱ ‹‹ታሪክ›› ጸሐፍት አንዱን ወክለህ አልያም ሆነህ የምትጽፍ ይመስላልና ምናልባት ደግመህ ብታየው፡፡ ሆኖም ታዲያ የቃላት ድርድር በዛበትና አሰለቸ፡፡ አንዱን ሳትጨርስ ወደአንዱ ትዘላለህ፡፡ መልክ አሳጣኸውና ግራ ለማጋባት ያደረግከውም መሰለኝ፡፡ ስለምን አንተ ያልከው ሁሉ ተቀባይነት እንዳለው እንዳሰብክም አላውቅም፡፡ እራስህን ግን ምን ይህል እንደምትወድ አስታውቆብሃል፡፡

ለዘመናት ከኦሮሞነት ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ማናቸውም የታሪክ ክርክሮች ማሳያ ተደርገው የሚነሱትን ‹‹አለቃ›› የሚል ቅጥያ የተሰጣቸው አድርባዮች የጻፉትን ይዘን እስከመቼ እንደምንዘልቅ አላውቅም፡፡ እነርሱ ላንተና ለመሰሎችህ እንዲመች አድርገው ባሰናዱት አይነት ሳይሆን፤ ሌሎች ምሁራን ደግሞ ጉዳዩን መርምረው ያሰፈሩትንም ማጣቀስ ተገቢ ይመስለኛል፡፡

በመሰረቱ፤ ዋናው አጀንዳ የነበረው የአኖሌ የመታሰቢያ ሐውልት ይመስለኛል፡፡ ይህ ደግሞ በእርግጥም ሰማዕታትን ለማሰብ የሆነ ስለሆነ መልካም ነው ብሎ ማለፍ ክፉ አያስብልም፡፡ ያንን ዕልቂት በቅጡ የሚያስታውሱት፤ ህመሙ የሚሰማቸው፤ ቁስሉ እስካሁን የሚኮሰኩሳቸው እኒያ የዛው አካባቢ ተወላጆችና፤ በዚሁ ዳፋ እልቂት ያስተናገዱት የአርሲ ልጆች፣ እናቶች፣ አዛውንቶችና መላው ማህበረሰቡ ነው፡፡ ስለሆነም ይሁነኝ ልጆቼን፣ ወንድሞቼን፣ እናቶቼን፣ አባቶችን፣ በአጠቃላይም ወገኖቼን ላስብ ያለው የአርሲ ብሎም የኦሮሞ ህዝብ ወገኖቹን ለማሰብ ለምን ይከለከላል? በመሠረቱስ አፍን ሞልቶ ተረት ነው ለማለት መድፈር ህዝብን ‹‹ታሪክህን አታውቅም›› ከማለት በምን ያለይ ይሆን?

የኦሮሞ ጥናት ማህበር እ.ኤ.አ. በ1995 ባሳተመው የጥናት መድብል ሁለተኛው ቅጽ ላይ አባስ ሀጂ (ዶ/ር) የአርሲ ኦሮሞ ህዝብ አጼ ምኒልክ ላይ ያሳየውን ፖለቲካዊና ወታደራዊ ጥንካሬ አስመልከቶ ባሰፈረው ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ ‹‹የአርሲ ህዝብ ለምን እና እንዴት ያን ያህል ብዛት ያለው ተዋጊ ኃይል ለረዥም አመታት በማንቀሳቀስ፤ ኢጣልያን በወቅቱ በአንድ ጦርነት ለመርታት የቻለውን ምኒልክን ለመuuም ተቻለው?›› የሚለው ጥያቄ ማንም ሊጠይቀው የሚችለው እንደሆነ ይጠቅሳል፡፡
በወቅቱም የአርሲ ኦሮሞ እራሱን ለመከላከል የወሰዳቸውን እርምጃዎች ያትታል፡፡ የምኒልክን አቅም በቅጡ የተፈተነበትም እንደነበር ያሳያል ይኸው ከላይ የተነሳው ጥያቄ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም ታዲያ አርሲዎችን ጠቅሞዋቸው ነበር ያላቸውን ምክንያቶች ዘርዝሮዋል፤ ከእነርሱ ውስጥም የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

የቦታውን አቀማመጥና አርሲዎች በዚህ ያገኙትን ጠቀሜታ በአንደኝነት እንደምክንያት ያነሳዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ተፈጥሮም ታዳላለች የሚባለው አይነት ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ታዲያ ምንም እን£ በርካቶች የአርሲ ህዝብ በወቅቱ በአዋሽና ሸበሌ ወንዞች መሐል ብቻ የሚኖር አድርገው ቢገምቱም፤ ከዛም ባሻገር አርሲ ከኦሮሞ ብሔር ውስጥ አንዱና ትልቁ ‹‹ቅርንጫፍ›› መሆኑን የዘነጉት ይመስላል፡፡ በዚህም መነሻነት የህዝቡ ቁጥር ከፍተኛ የነበረ መሆኑም አግዞታል ማለት ነው ይለናል ዶ/ር አባስ፡፡

የውስጥ ሰላምና አንድነቱ ለአርሲ ሌላኛው ጥንካሬው ነበር፡፡ ወራሪውንም በብርቱ የሞገተው ለዛም ነው፡፡ እንደጎረቤቱ ቦረና የውስጥ ሽኩቻ አልነበረበትም፡፡ በአንድ ወቅት እንደውም በተለይም ከቀደምቶቹ መካከል የሆኑት ቃቃ ኦሮሞ በሰጡት ትዕዛዝ መሠረት ኦሮሞ ኦሮሞን እንደማይገድልና አርሲም ለዚሁ ትዕዛዝ ተገዢ እንደነበር ያነሳል ዶ/ሩ፡፡ ሆኖም፤ እንደሌሎቹ የኦሮሞ ታሪኮች ሁሉ ይህም ታሪክ በጊዜ ሂደት እንዲጠፋ ሆነ፡፡

ተያይዞም፤ አርሲ ምንም እን£ በጎሳ የተለያየ ቢሆንም ለወራሪና ሌላ ባዕድ ሊነካው ሲሞክር በአንድነት ሆኖ ይመክት እንደነበርና ለዚሂም ያሳይ የነበረውን መነሳሳት ነው ጥናቱ የሚያወሳው፡፡
በአርሲ ወገን ሆነው ህዝቡን ሲያስተባብሩና አመራር ሲሰጡ ከነበሩት መካከል በጥናቱ ሶስቱ ተጠቅሰዋል፡፡ እነርሱም፤ ሱፋ ቁሶ፣ ሌንጂሶ ዲጋ እና ሮባ ቡታ ናቸው፡፡ እኒህ ጀግኖች ታዲያ በአልደፈርም ባይነት ለህዝብ ጥቅም የተዋደቁ ናቸው፡፡ በእነርሱ መሪነት በሺዎች የሚቆጠር የአርሲ ኦሮሞ ላለመወረር ሲል ህይወቱን ሰጠ፡፡ እኒህ ግለሰቦች ጥሩ የጦር መሪዎች፤ ፖለቲከኞችና ህዝብን መምራት የሚችሉና የቻሉ ነበሩ በወቅቱ፡፡ የአርሲን ብርታት ያየው ምኒልክ ታዲያ ያለርህራሄ ሁሉንም ባሻውና ይጠቅመኛል ባለው መልክ አደረገ፡፡ ጭፍጨፋው ዘግናኝ እንደነበር መዛግብት ያወሳሉ፡፡ አንተ እንደምትለው አይደለም፤  ደብተራ አምሳሉ፡፡ ነገሩ ብርቱ ነው፡፡
በአንድ አጋጣሚም ስለመገንጠል አንስትሃል፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ትግልና ጥያቄ ሲነሳ ለምን ከመገንጠል ጋር ብቻ ተያይዞ እንደሚነሳ አላውቅም፡፡ ይህም ስህተት ነው፡፡ ለአሁን እንተወውና በሌላ ጊዜ ካልሆነ እመለስበታለሁ፡፡

ለማንኛውም፤ጸሐፍት ተብለው የሚነሱትን ሰዎች አስመልክቶ ነጋድራስ ገ/ህይወት ባይከዳኝ፤ ከዚህ በፊት በሌሎች ጽሁፎቼም እንዳነሳሁት በወቅቱ (ያን ጊዜ ማለት ነው) የነበሩትን ጸሐፍት ለሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚገባ በአንድ መጽሐፋቸው ላይ ጥሩ አድርገው ገልጸውታል፡፡ ሲያብራሩም የመጀመሪያዎቹን ሊቃውንት ቤተመንግስት ሲላ;ቸው፤ እንጀራን ሲፈልጉ ከቤተመንግስት ተጠግተው በንጉሱ የታዘዙትንና ንጉሱን የሚያወድሱ ነገሮችን ታሪክ ብለው በመጻፍ ለላው ትውልድ የሚያስቆዩ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ መነኮሳት መሆናቸውን ይጠቅሳሉ፡፡ መነኮሳቱ የሚጽó<ቸው ታሪኮች አድልዎ ይበዛበታል ሲሉ ያስረዳሉ፡፡ እራሳቸውን ለማዋደድ ሲሉ የወቅቱ ‹‹ተዓማኒነታቸውን›› ተጠቅመው ታሪክ ብለው የእራሳቸውን የውስጥ ጥላሸት ታሪክ ብለው አስፍረውታል፡፡ የራሳቸውን እንጂ የህዝቡን ጥቅምና ጉዳት ከቶ አይቆጥሩምና፡፡ ስለዚህ የልባቸውን የሚፈጽምላቸው ንጉስ ቅዱስ ይሉታል፡፡ ከድንቁርናቸው ወጥቶ ከፍ ባለ ህሊና ተመርቶ ስለዜጎቹ ልማት የሚጥር ግር እርኩስ፡፡ አንተስ ደብተራ አምሳሉ እንዴት ትላቸው ይሆን?

ሌላውና በጣም ገራሚው ነገር ደግሞ የሐይማኖት መዛግብቱም ውስጥ ጉዳዩ እንዲካተት መሆኑ ነው፡፡ ይህንን በማድረግ ሀይማኖቱንም ሌላ መልክ ለማስያዝ ይጥራሉ፡፡ በጣም የሚገርመው ታዲያ ስለጉዳዩ አቶ አጽመ ጊዮርጊስ የተባሉት ግለሰብ በአንድ ወቅት ያሰፈሩት ከዚህ እንደሚከተለው ነው፡፡ ‹‹በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን ጋላ ሁሉ ተገዛ፤ ባማራ ሕግና ሥርዓት ሄደ፤ ካህናቱ ግን አንድ ጋላ አስተምረው አላጠመቁም፡፡ ይልቅስ ተፊተኛው ቂም የበለጠ ቂም በልቡ አኑረውበት መሬቱን በቀላድ ወሰዱበት፡፡ አንድ ቀላድ የቅስና አንድ ቀላድ የአወዳሽ እያሉ በዚሁ ስብከት ንጉሱን አሳመኑ፡፡ ስለመንግስት ያሰቡ መስለው ለንጉሱም አንድ ቀላድ፣ ለገባር አንድ ቀላድ፣ ለወታደር አንድ ቀላድ....መሬቱን ተካፍለው ጋላን አንደባርያ አድርገው ይገዙታል እንጂ የክርስቶስን መንገድ አላሳዩትም፡፡ እነሱም አልተማሩም፡፡ አስተማሪው ቢመጣ ይከለክላሉ፡፡ ከትልቁ ሁሉ ከንቱ ብላሽ የሚያደርገው በቁጥርም እርሱም እግዚአብሔርን አለማወቃቸው ነው፡፡ ማለት ሕጉንና ትእዛዙን በሁሉም ስፍራ መኖሩን አያውቁም፡፡››

አየህ አይደል ደብተራ አምሳሉ? ይህም የአንተና የእኔ የኢትዮጵያ ታሪክ ነው ተብሎ ይጻፋል፡፡ እነዚህንም እናነባለን፡፡ አንተ ላንተ የሚመች የመሰለህን መሰል ነገር ታሪክ ነው ብለህ ልትሞግተኝ ትሞክራለህ፤ ብለህ ደግሞ ታሪክ ከእኔ ወዲያ ለማለትም ትዳዳለህ፤ እኔ ግን ልልህ ወድጃለሁ፤ በመሀከል ያለችው ግን ኢትዮጵያ ናት፡፡ ይህች ኢትዮጵያ ደግሞ እውነቱን አፍረጥርጠን ለጠፋውም ለለማውም የሆነውን ሁሉ ተነጋግረን አውቀን፤ እውነተኛውን ነገር እስካልያዝን ድረስ ዝም ብለን ተነስተን፤ የምንደነፋባት መሆን የለባትም፡፡

የተመቸንን በሰማን ቁጥር ‹‹እውነቱ ይሄ ነው›› ብለን በምንለው ልክ፤ እውነቱን ስንሰማ ታወቀብኝ በሚል ስሜት ከምንንደረደር፤ ሀገራዊውን የቆሸሸ ታሪክ አምኖ ተቀብሎ ወደፊት ስለማይኖረን ወይም እንዳይኖረን ከምንመርጠው መጥፎ ታሪክ ላይ ብንሰራ መልካም ነው፡፡ ‹‹ከእዛ ዘመን ደብተራ የዚህ ዘመን ደብተራ›› ብለን እንድንናገር አድረገን፡፡



አብርሃም ተስፋዬ