2014 ሴፕቴምበር 25, ሐሙስ

ወይ አንቺ!

‹ደግሞ በእድሜሽ እንጣላ?›

ሠሞንኛ አጀንዳ ሆነሻል፡፡ በርካቶች እድሜሽን ሲጠይቁ እየሠማሁ ነው፡፡ አንዳንዱም ታሪክ ቀመስ ጉዳዮችን አክሎ ‹‹ይኸውላችሁ እወቋት የሚባለው ሁሉ ውድቅ ነው›› ይላል፡፡ ሌላውም ይህንኑ በመንተራስ ‹‹እርሱን በፍጹም አትስሙ/አትመኑ፤ እውነቱ ይህ ነው›› ይላል፡፡ ብዙ ጽሁፍ፡፡ በዚህ መካከል ነው ታዲያ የፌስቡክ ወዳጄ ሽንቁጥ አየለ ‹‹ኢትዮጵያዊ ውህድ ህዝብ ነው? የጋራ ኢትዮጵያዊነት ማንነት ያለውስ ህዝብ ነው?›› ብሎ የጠየቀበትን ጽሁፍ ያየሁት፡፡ እናም አነበብኩት፡፡ አንብቤም ዝምታን ለመምረጥ ተቸገርኩ ስለሆነም እንዲህ እጀምራለሁ፡፡ በቅድሚያ ግን ምስጢር፡፡

እንዳይገርምሽ፡፡ አንቺ ማለቴም እንዳይከፋሽ፡፡ በ‹አንቺ› የሚጠራኝ ይጠየቅልኝ ካልሽ ዘላለምን (ዘላለም ክብረት) ጠይቂው፡፡ ለምን አንቺ እንዳለሽ በቅርቡ ከእስር ቤት ጻፈው በተባለ ጽሁፉ ተንትኖልን ነበር፡፡ እንደውም ‹ይድረስ ላንቺ› ብሎ የጻፈልሽ ደብዳቤ፡፡ መቼም አንብበሽዋል አይደል ኢትዮጵያ? እኔም ተቀበልኩትና ‹አንቺ› አልኩሽ፡፡ አንቺ ደግሞ! አንቺ!
ሸንቁጥ አየለ በጽሁፉ በርካታ ነገሮችን አንስቶ ነግሮናል፡፡ ደጋግሜ አንብቤዋለሁ፡፡ በእርግጥ ጥቂት የማይባሉ የቃላት ግድፈቶች ያዝ አላደረጉኝም ለማለት አይደለም፡፡ ቢሆንም አንብቤዋለሁ፡፡ ስላንቺ እድሜ ጀመረና፤ ስለማንነትም አንስቶ ውህደትን ሰበከ፡፡ መልካም ሀሳብ ይመስላል፡፡ ነገር ግን አቀራረቡ ትንሽ ተቀላቀለብኝኛ ነው፡፡

‹አንቺ ደግሞ እድሜሽ?

በእርግጥ በእድሜሽ ዙሪያ በርካታ የተዘበራረቁ እይታዎች እንዳሉ አንብቤያለሁ፡፡ እናም ይህንኑ ለመረዳት ሞክሬያለሁ፡፡ ክርክሮችም አሉ፡፡ በእድሜሽ ልኬት መጠን ላይ ብዙዎች የራሳቸውን ማሳመኛ እያነሱ ይከራከራሉ፡፡ በእውነት ግን እድሜሽ ስንት ነው?

እኔ ሳስብ አንቺነትሽን ለመውሰድ በእርግጥም የተወሰኑ የኋላ ታሪክሽን ማንሳት ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ እርሱን ደግሞ ካነሳን፤ ከድሮ ጀምሮ ስንማር እንደመጣነው እውነት ለመናገር አርጅተሻል፡፡ የነአክሱም፤ የነላሊበላ፤ የነጀጎል፤ የነፋሲለደስ፤ የነሼከነሁሴን፤ የነአዋሽ መልካ፤ የነጃሺ፤ ………………………………… ታሪክ ማገላበጥ ምናልባት ቀላል ሊሆን ይችላል፡፡

ዕድሜሽ ታዲያ ክርክር ውስጥ የሚገባው አሁን የያዝሽውን ቅርጽ አስመልከቶ ከሚሰጡት ማብራሪያዎች በመነሳት ነው፡፡ ‹ይህንን ቅርጽ የያዘው በዚህ ወቅት ነውና እድሜሽ እዚህ ላይ ነው› ብለው አንዳንዶች በመቶዎች ብቻ የተወሰነ እንደሆንሽ ይናገራሉ፡፡ እኔ ደግሞ አሁን የያዝሽን ቅርጽ የያዝሽው የግዛት ማስፋፋትን ተከትሎ ቢሆንም እንኳ ያው አምነሽ የተቀብለሽው የራስሽ ታሪክ ከሆነ፤ ነገር ከውልደት ይጀምራልና እድሜሽ ሄዷል አሮጊት ነሽ እልሻለሁ፡፡ በዚህም እርጅናሽ እስማማለሁ፡፡ እድሜሽ የበረከተ ነው፡፡ የሆንሽ ባለብዙ እድሜ ነገር ነሽ፡፡ ነገር ግን አባቶች የሚሉትን ልዋስና ከእድሜሽ አልተማርሽም፡፡ ነገር ግን በእድሜሽ ልክ አይደለሽም፡፡ ነገር ግን እንደእድሜ እኩዮችሽ አይደለሽም በታናናሾችሽም ልክ ለመሆን ገና ገና ይቀርሻል፡፡

ታሪክሽ

ከእድሜሽ ጋር ተያይዞም ታዲያ ታሪክሽ እንደተፈለገው የሚጠመዘዝ አይነት ነው፡፡ ሁሉም ያሻውን የሚልሽ፤ ሁሉም በልኩ ሊሰፋሽ የሚችል አይነት ነሽ፡፡ ደግሞ እኮ የሚገርመው ዝምታሽ!
በአንቺ ዝምታ ውስጥ ትዝብት ይታያል፡፡ በዝምታሽ ውስጥ ንቀትም አለ! ዝምታሽ አንዳንዴ ያስፈራል፡፡ ዝምታሽ አንዳንዴ ያስጠላል፡፡ ዝምታሽ………….በዚህ ብርቱ ዝምታሽ ውስጥ ደግሞ ታሪክሽን እናውቃለን የሚሉ እንዳሻቸው ሲያደርጉት ይስተዋላል፡፡

ሸንቁጥ ታዲያ ለጽሁፉ የጠቀሳቸው ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስኃቅ በአንድ ወቅት (ወቅቱን አልጠቀሰውም) ‹የማንነት ግጭት ውስጥ የገባው የዚህ ዘመን ትውልድ› ብሎ በገለጸው የእኛ ትውልድ አባላት ኢትዮጵያ ያላትን እድሜ አስመልከቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሰጡት ያለው መልስ እንዲህ የሚል ነበር፡-

‹‹ የኢትዮጵያ ታሪክ ከ10ሺህ አመታት በላይ ነው፡፡ በዚህ ረዥም የታሪክ ሂደት ውስጥም የኢትዮጵያ ህዝብ ውህድና የጋራ መሠረታዊ እሴት ያለው ህዝብ ነው…››

እንደሸንቁጥ ጽሁፍ ከሆነ ፕሮፌሰሩ ንግግራቸው በዚህ አላበቃም፡፡ ‹‹የአሁኑ ትውልድ ታሪኩን በደንብ ከመረመረ በርካታ የሚያስተሳስረው አኩሪ ታሪክ የሚያገኝባቸው ታሪካዊ ኩነቶች አሉት›› ብለዋል ፕሮፌሰሩ፡፡

በእርግጥ የፕሮፌሰሩ ሀሳብ መልካም ነበር፡፡ ብዙ ታሪክ እንዳለሽ ይነገራል፡፡ ነገር ግን ይህንን ታሪክ ለመመርመር የሚያስችል ምቹ ሁኔታ አለ? እውነት አሁን ያለውና ያንቺ ነው የሚባለው ታሪክ ሁሉንም ዜጎችሽን ያካትታል? በቀደሙት ዘመናት የተከወኑ እኩይ ተግባራትስ የታሪክሽ አካል አይደሉም? መልካም መልካሙን እንጂ ሌላውን በተደራጀ መልኩ ማግኘት ይቻላል? የታሪክ ምሁሮች የሆኑ ልጆችሽስ ምን ያህል ለሙያቸውና ላንቺ የታመኑ ናቸው? ታሪክ አዋቂዎችሽም ጥያቄ ውስጥ የሚጥላቸው ነገር ሲከውኑ ይስተዋላል አኮ! ታሪክሽ እኮ እንዲሁ እንዳወዛገበ ዘለቀ፡፡ ለዚሁም ራስሽ ታሪከኛ ሆንሽ ማንን እንመን ታዲያ? አንቺ ስለምታውቂያቸው ንገሪን፡፡

‹ታላቋ›

ሙገሳ ቀለብሽ ነው መቼም፡፡ የበርካታ ልጆችም እናት ነሽ፡፡ የሠሩልሽ ግን እምብዛም ነው፡፡ ‹‹የታላቋ….›› እያሉ ይሸውዱሻል፡፡ ‹ታላቅ›ነትሽን ለማብሰር በአደባባይ ለመመስከር አይቦዝኑም፡፡ ዞር ብለሽ እያቸውማ………… የሉም፡፡ አንድም አውቁሽም……………… አልያም………… አጋጣሚው ስለፈጠረላቸው ብቻ ‹ታላቅ› ምናምን እያሉ ሊሸውዱሽ ይሞክራሉ፡፡
ስለቀደመውም ዘመን ሲነሳ በእርግጥ ሥልጣኔ የሚሉትን ነገር ያነሳሉ፡፡ ነገር ግን በብዙ አጋጣሚ ጦረኛ ልጆችሽ እና የጦር ሠራዊት ብዛታ ከሁሉ ገዝፎ ይታያል፡፡ ሸንቁጥ እራሱ መዛግብቱን ጠቅሶ ስለታላቅነትሽ ሲወሳ ‹‹……… አንድ ሚሊዮን ሠራዊት አዝምታ……›› ‹‹………እስራኤልን መውረሯ………›› አክሎም እስራኤላውያን ይፈሩሽ እንደነበር አውስቷል፡፡ ሲቀጥልም የእስራኤል ነገስታትና የታሪክ ጸሐፊዎች ስላንቺ ሲጽፉ ‹‹ታላቂቷ›› ‹‹ታላቅ›› ይሉሽ እንደነበር ነግሮናል፡፡ እንደውም በአንድ ወቅት የእስራኤልን ንጉስ ለመውጋት ሄደሽ እንደነበር ነግሮናል፡፡ ኧረ እንደውም በአንድ ወቅት የእስራኤልን ንጉስ ለመውጋት ሄደሽ የሠራዊትሽን ብዛት አይቶ የእስራኤሉ ንጉስ ወደእግዜአብሔር መጮሁንም መዛግብት አጣቅሶ ነግሮናል-ሸንቁጥ፡፡
ታዲያ እኒህን አንስቶልሽ ሲያበቃ ነው አንቺ ሆይ ወጣት አይደለሽም ያለሽ፡፡ በመሠረቱ ከእርጅናሽ ያተረፍሽውን እጠይቅሻለሁ እኔ፡፡ ስለምን እንዲህ ሆንሽ? ግድየለሽም ንገሪኝ፡፡

‹ውህድ›

ልጆችሽ ውህድ ናቸው ይልሻል ሸንቁጥ፡፡ እርሱ ራሱ የጠቀሳቸው ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅም ይህንን ሃሳብ እንደሚጋሩ ለመረዳት ችያለሁ፡፡ ነገር ግን የጋራ ነገር አለን ማለት ውህድ መሆን ነው ? እውነቱን ለማወቅ ጠየቅኩሽ፡፡ በተለይ በጽሁፉ ሸንቁጥ ውህደት ከድምር ይበልጣል ብሎሻል የሂሳብ ሊቃውነቱን አባባል ወስዶ፡፡ አንቺ እንዴት ታስቢያለሽ?

እኔ ግን እንደሚመስለኝ በርካታ ልጆች አሉሽ፡፡ የእነዚህ ልጆችሽ ልዩነት አያፈርስሽም፡፡ የተዋሃዱ ልጆች አሉሽ መባሉም አንድ አያደርግሽም፡፡ እንደውም ሲመስለኝ ይህ የመዋሃድ እሳቤ እንደተዳፈነ ፍም ሆኖ ይጎዳሻል፡፡ በአንድ እይታ ብቻ እንድትወሰኚ ያስገድድሻል፡፡ ስለሆነም በዚህ የማይስማሙ ልጆችሽ ደግሞ ወደዚህኛው እንዲመጡ ብርቱ ስራ ይጠብቅሻል፡፡ እንዲያው በደፈና ውህድ ነን ቢባል አንቺስ ደስ ይልሻል?

ባይሆን ያንቺን የጋራ እናትነት መካድ ከባድ ነው፡፡ ይህም ቢሆን ታዲያ ልጆችሽ ላይ ይለሽ የምልከታ ልክ መታየት ይኖርበታል፡፡ በእርግጥ ቢለያዩም ሁሉንም በተቻለ አቅም ሊያስማማ የሚችል-መቻቻል፤ ሠው የመሆናቸውን ልኬት-እኩልነት ለማምጣት ብትሠሪ ይሻልሻል፡፡ እኔ እንዲህ ይሰማኛል፡፡

ይህንንም ስልሽ ግዛት ለማስፋፋት ሲባል ነገስታቱና መሳፍንቱ በየወቅቱ ያደረጉት ውጊያ እንዳለ ሆኖ የነገስታቱን ፍላጎት ብቻ ባማከለ መልኩ የተካሄደውንና ‹ተሸናፊው› ህዝብ የደረሰበትን የታሪክ፤ የሥነልቦናና የማንነት ‹መነቅነቅ› ግን የሚዘነጋ አይመስለኝም፡፡ በእርግጥ አንቺም እንደማትዘነጊው አስባለሁ፡፡ በዚህ መካከል ‹ወራሪ› እና ‹ተወራሪ› ብሎ ማሰብ ይኖር ይሆናል፡፡ አሁን ጉዳዩ የመውረርና የመወረር ሳይሆን ከዚያ ባሻገር ነገስታቱ የወሰዱት እርምጃዎች፤ በሚወሩት ህዝብ ታሪክ ላይ ያሳረፉት ነገር ሁሉ በትክክል መነገር፤ መተረክም እንዳለበት አስባለሁ፡፡ ይህ ሲሆን አንቺነትሽ እውነት ላይ የተመሠረተ፤ እውነትሽ ገኖ የወጣ ይሆናል፡፡ ካለሆነ ለወደፊት ለልጆችሽም ፈተና እንዳትሆኚ እሰጋለሁ፡፡

እንዲህ ያለውን ታሪክም ቢሆን በግልጽ ተወያይቶ መግባባት ላይ ቢደረስ የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡ ለነገሩ አንቺ ‹‹ስንቱን ሰብስቤ?›› ትይኝ ይሆናል፡፡ ግን ብትሞክሪው መልካም ነው፡፡ እኔ እንደውም ከውህድሽ ይልቅ በልዩነት ውስጥ በሚኖረው የልጆችሽ መስተጋብር ውስጥ መከባበርና መደጋገፍ ያለው ድምቀትሽ ይናፍቀኛል፡፡

ለዛሬ እንዲህ ብልሽ አይከፋሽ ይሆናል፡፡ ሸንቁጥ በማንነት ጉዳይ ላይ ስለተነሳው ሁነት ደግሞ በሌላ ጊዜ ልመለስበት፡፡

መልካም ይሁን፡፡


© አብርሃም ተስፋዬ

http://shenkutayele.wordpress.com/2014/09/24/%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB%E1%8B%8A-%E1%8B%89%E1%88%85%E1%8B%B5-%E1%88%85%E1%8B%9D%E1%89%A5-%E1%88%8A%E1%89%A3%E1%88%8D-%E1%8B%AD%E1%89%BD%E1%88%8B%E1%88%8D-%E1%8B%A8%E1%8C%8B/

2014 ሴፕቴምበር 7, እሑድ

ይድረስ ለወዳጄ - በዘላለም ክብረት

የኔ ፅጌረዳ  ሰላም ላንቺ ይሁን! እንዴት ነሽልኝ? ባለፈው የፃፍኩልሽን ቧልታይ የበዛበት ደብዳቤ አነበብሽው ይሆን? ዛሬ ደግሞ ስለክሴ፣ ስለከሳሼና ስለአጠቃላይ ሁኔታዎች ልጽፍልሽ አሰብኩ፡፡ እንግዲህ በዚህ ደብዳቤ ትንሽ ኮስተር ሳልል አልቀርምና ከወዲሁ ይቅርታን እለምናለሁ፡፡

ግርምቴ
ከታሰርኩበት ሚያዝያ 17/2006 ጀምሮ በጣም ሲገርመኝ የነበረው ነገር የፖሊስ/የመንግስትና የሕግ ታላቅ እኩያ ከተያዝኩበት ደቂቃ ጀምሮ አውቆ በሚመስል መልኩ የተለያዩ የፍትሕ አካላት እያንዳንዱን የሕግ አንቀፆች በተግባር ሊጥሷቸው ማየቴ ነበር፡፡
 
ለሕጎቹና ለሕግ አካላቱ ቅርብ በመሆኔ ምክንያት የመንግስት አካላቱ ይወስዷቸው የነበሩትን የተለያዩ ርምጃዎች በሕጉ አይን በማየቴ ሊሆን ይችላል የሕግ ጥሰቱ እጅግ ጎልቶ የታየኝ፡፡

የፍተሻ ፈቃድ (Search Warrant) ከእስር ማዘዣ (Arrest Warrant) ጋር በአንድ ወረቀት ላይ ተደባልቆ በመምጣቱ ገና ከመታሰሬ ነው የሕጉ ነገር ያሳሰበኝ የጀመረው፡፡ ሕግ ስንማር የፍተሻ ፈቃድ ከእስር ማዘዣ ተለይቶ እንደሚመጣ፣ በፍተሻ ፈቃዱ ላይ ሊፈተሽ የተፈለገው ነገር በግልፅ ሊቀመጥ እንደሚገባ፣ ፍተሻ ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት መከናወን እንዳለበትብንማርምፖሊስበታሰርኩበት ወቅት አንዱንም የሕግ አንቀፅ ላለማክበር ያሰበ በሚመስል መልኩ የፍተሻ ፈቃድን ከእስር ፈቃድ ሳይለይ፣ ፍተሻውን ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ በመጀመር፣ በፍተሻው ምን ማግኘት እንደሚፈልግ የማይገልፅ የፍተሸ ፈቃድ በማሳየትና እኔ ስጠይቅም ለመናገር ፍቃደኛ ባለመሆንሕጉንንዶ ንዶየኔን የግለሰቡን መብቶች በዜሮ በማባዛትወንጀልን የመከላከል እርምጃውንጀመረ፡፡ በፍተሻ ወቅት የሚፈለገው ነገር ምንነት አለመገለፁም ፖሊስለጠረጠረኝሕገ-መንግሥቱንና ሕገ-መንግሥታዊ ስርዓቱን በኃይል፣ በዛቻና በአድማ የመናድ ወንጀል እንደ ኤግዚቢት የያዛቸውማስረጃዎችምንነት ይገልጣቸዋል፡፡
በፍተሻ ወቅት ፖሊስ ከቤቴ በኤግዚቢትነት ከያዛቸውእቃዎችመካከል 90 በመቶው ገበያ ላይ ያሉ መጽሐፍት ሲሆኑ ከነዚሀም መካከል Paulo Coelho “By the river paedra I set down and wept’ PV.I.Lenin ‘what is to be done’ የአፄ ሱስንዮስ ዜና መዋዕል፣ የፍቅረስላሴ ወግደረስእኛና አብዮቱ›… ጨምሮ ሌሎች መፅሀፍት የሚገኝበት ሲሆን፤ የተለያዩ የሙዚቃ ሲዲዎችም በኤግዚቢትነት ተይዘዋል፡፡

(
የሚገርመው ፍተሻው ሕገወጥ መሆኑንለፖሊስበተደጋጋሚ ብናገርምብርበራ ከጀመርን በኋላ ልናቋርጥ አንችልም የሚያስፈልገንን ነገር አንተ ልትነግረን አትችልምየሚሉ መልሶች በመስጠትአዲዮስ ሕግየሚል አሰራር ከመከተላቸውም በላይ በቤቴ የተገኘ እንደአዲስ ራእይአይነት መፅሄቶችን የብርበራው መሪ የሆኑ ግለሰብ ለበታች መርማሪዎችተዉት እሱ የኛ ነውየሚል አመራር እየሰጡ ግርምቴን አብዝተውት ነበር፡፡ ጉዳዩን አስቂኝ የሚያደርገው ደግሞ በፍተሸው ወቅት ቤቴ ውስጥ ከተያዙትኤግዚቢቶችመካከል አንዱም እንኳን ለክስ ማስረጃ ሁነው አለመቅረባቸው ነው፡፡ ይህ ነው እንግዲህ ለህግ /ቤት ‹search is not a fishing expedition in which the police grabs every thing › ተብለን የተማርነው፡፡)

የእስርና የምርመራ ጊዜ ደግሞ ፖሊስ ሕጉን ለመጣስ ሆን ብሎ የተጋ በሚያስመስለው መልኩ ሕጉ ግድ ሳየሰጠው የፈለገውን ሲያደርግ የከረመበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ ወቅት ነውእኛ የሚያሳስበን የአንተ የአንድ ግለሰብ መብት ሳይሆን፣የሰማንያ ሚሊዮን ሕዝብ ደህንነት ነውየተባልኩት (ውዴ! Ayn Rand እንኳንም ይሔን ሳትሰማ ሞተች አላልሽም?)፡፡ በዚህ ወቅት ነውየሽብር ሕጉን ጥርስ አውልቃችሁ አምጡ የሚለን ከሆነ ጥርስ ከማውለቅ ወደኋላ አንልምብሎ ፖሊስ ሕገ-መንግስቱንና የዜጎች መብትን በአንድ ላይ ሲቀብራቸው የተመለከትኩት፡፡ (‹ሕገ -መንግስቱ የሀገሩ ህጎች በሙሉ የበላይ ሕግ ነውየሚለው የህገ መንግስቱ አንቀፅ በምድረ በጋ የተደነገገ እንደሆነ ግንዛቤ ለመጨበጥ ችያለሁ)፡፡ በዚህ ወቅት ነው፡ የፍርድ ቤቱ ትእዛዝ እንዲፈፀምልኝ ለጠየኩት ጥያቄሂድ ከዚህ!የማነው?! ፍርድ ቤት ማነው እኛን የሚያዘው? ከፈለገች ዳኛዋ ራሷ ትፈፅምልህ…› የሚል መልስከህግ አስከባሪ ፖሊስየተሰጠኝ፡፡
            ‹‹
ምን አይነት ዘመን ነው የተገላቢጦሽ፤
           
አህያ ወደ ቤት፣ ውሻ ወደግጦሽ፡፡
ይሏል እንዲህ ነው፡፡ በዚህ ወቅት ነው፤ ምንም አይነት ሕጋዊ መብቶቼ ሳይነገሩኝለምርመራ የተቀመጥኩበትና ብሎግ ላይ የተፃፉ ፅሁፎች የእኔየእምነት ክህደትቃል እንደሆኑ ተደርገው መፃፍ እንዳለባቸው ትእዛዝ የተሰዘጠኝና በእምነት ክህደት ቃሌ ውስጥ ወይጥፋተኛ ነኝማለት አለያም ባዶውን መተው እንጂጥፋተኛ አይደለሁምየሚል ነገር መስፈር እንደማይችል የተረዳሁትናለምን?› ብዬ ስጠይቅምከበላይ አካል የመጣ ትዕዛዝእንደሆነ የተነገረኝ፡፡ (ማሬ፣ ዕድለኛ ባልሆን ኖሮ እንደአንድአባሪዬህገ መንግስቱ ተከብሮ እያለ፣ ሕገ-መንግስቱ ይከበርበማለቴ ጥፋተኛ ነኝብለህ ፈርም ተብዬ መከራዬን አይ ነበር፡፡)በዚህ ወቅት ነው፤ መንግስቴ በመጀመሪያበሽብር ወንጀልባይጠረጥረኝም የፀረ-ሽብር ሕጉ አንቀፅ 14 በሚያዘው መሰረት ስልኬን ከግንቦት 2005 . ጀምሮ በመጥለፍ ንግግሬን ሁሉ ሊያደምጥ እንደነበር የተረዳሁትና ‹‹እንዴየሽብር ተግባራትን ለመፈፀም የማሴር ወንጀልየተጠረጠርኩት ከታሰርኩ 23 ቀናት በኋላ ነው፤ ይሄም ፖሊስ እስከታሰርኩበት 23 ቀን ድረስ በሽብር ጉዳይ ምንም አይነት ጥርጣሬ ያልነበረው ሲሆን ታዲያ ስልኬን አንድ አመት ለሚሆን ጊዜ እንዴት የፀረ ሽብር-ሕጉን ጠቅሶ ሊጠልፍ ቻለ?›› ብዬ ለጠየኩት ጥያቄ መልሱ ዝምታ እንደሆነ የተረዳሁት፡፡ (በነገራችን ላይ ስልኬ ለረጅም ጊዜ ቢጠለፍም ለማስረጃነት የቀረበብኝ ከአባሪዎቼ ጋርሻይ-ቡና እንበል እስኪ ብለን ያወራናቸው ወሬዎች ሲሆኑ፤ካንቺ ጋር ያውራናቸው ወሬዎች በማስረጃነት ባለመምጣታቸው ቅር መሰኘቴን በዚህ አጋጣሚ እገልፃለሁ፡፡) 

  
ግርምቴ ብዙ ቢሆንም እንዳይሰለችሽ በማሰብ አንድ የመጨረሻ ግርምቴን ልንገርሽና ሌላ ጉዳይ ላይ እናልፋለን፡፡ የእስር፣ የምርመራ፣ የብርበራሁሉ ዓላማ ተጠርጥረው የተጠረጠረበትን ወንጀል የሚያረጋግጥ መረጃ ለማግኘት ቢሆንም ከሁለት ወራት ለሚበልጥ ጊዜ፣ እጅግ የተራዘመ ምርመራ ተደርጎብኝ የቀረበብኝን ክስ ስመለከት ብዙ ነገሮች አስገረሙኝ፡፡ ቀዳሚው ጉዳይ የተከሰስኩበትንየሽብር ተግባር ለመፈፀም የማሴር ወንጀልበሚመለከት በምርመራ ወቅት አንድም ጥያቄ ያልቀረበልኝ ሲሆን፤ ይሄም ነገር ታዲያ የምርመራው አላማ ምን ነበር? እንድል አድርጎኛል፡፡ ሌላው ገራሚው ጉዳይ የሀገሪቱ ከፍተኛ የምርመራ ሂደት እንዲህ ቧልትና እያንዳንዱን እንቅስቃሴውን ከሕጉ ጋር በመላተም እንደሚያከናውን መገንዘቤ ነው፡፡ ታዲያፖሊስህግን ለመጣስ ካለው ትጋት የበለጠ ምን አስገራሚ ነገር አለ ውዴ?!

 The Fridgegate Scandal
እና ሌሎችም

እኔ አሁን ደግሞ ወደ ክሴ ልውሰድሽ እስኪ ክሴን ባጭሩ ለማስረዳት ያክል (ምንም እንኳን ክሱ ግልፅ ባይሆንም፣ እኔ እንደመሰለኝ)የሽብር ቡድን በማቋቋም (ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ለማድረግ የሚልምይመስላል›)በሀገር ውስጥ የተለያዩ የሽብር ድርጅቶችን (ሰውን ለመግደል የሕብረተሰቡን ጤና ለከፍተኛ አደጋ ለማጋለጥ፣ እገታ ወይም ጠለፋ ለመፈፀም፣ ንብረት ለማውደም፣ በተፈጥሮ፣ በታሪካዊና በባሕላዊ ቅርሶች ላይ ጉዳት ለማድረስ፣ የህዝብ አገልግሎቶችን ለአደጋ ለማጋለጥ ወይም በቁጥጥር ስር ለማዋልና ለማበላሸት) በመዘጋጀት፣ በማሴር፣ በማነሳሳትና በመሞከር የሚለው የመጀመሪያውና ዋነኛው ክሴ ሲሆን፤ሁለተኛው ክሴ ደግሞ ያች የፈረደባትሕገ-መንግስትንና ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን የመናድ ወንጀል ነው፡፡
           
ሁለቱም ክሶቼ የቅጣት ጣሪያቸው እስከ ሞት ድረስ መሆኑን መግለፄም አያስከፋሽም ብዬ አስባለሁ፡፡ (ዘጠኝ ሞት መጥቶ ከደጅ ቁሟል ቢለው፣ ስምንቱን ተውና አንዱን ግባ በለውአለ የሞት ዳኛ፡፡ እንደዳኛውአንዱን ሞት ግባብዬ ከመጋበዜ በፊት ብዙ የማጫውትሽ ጉዳይ አለኝና አስኪ ተከተይኝ ውቤ)

ከሳሼየሽብር ተግባራትንልፈፅም እንደተዘጋሁና እንዳሴርኩ እንዲሁምሕገ-መንግስቱንና ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድእንደሞከርኩ ለማስረዳት ያቀረቡልኝ የማስረጃ ዝርዝርን ስመለከት ግን የአሳሪዎችን ፍላጎትወዲህመሆኑን የተረዳሁት፡፡

በምርመራ ወቅት አንድም ጥያቄ ያልቀረበልኝየሽብር ድርጊትዋናወንጀሌሁኖ ሲመጣ አሳሪዬ ጋር ያለው ፍላጎት ሙሉ ለሙሉ የወንጀል እንዳልሆነ ያስረዳኝ ሲሆን፤ በሰነድ ማስረጃነት ከቀረቡብን ብዙ ገራሚና አስቂኝማስረጃዎችመካከልየሽብር ተግባራትን ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር በመሆን ለመፈፀም እንዳሴርንያስረዳል ተብሎ የቀረበው ዋነኛና ብቸኛ ማስረጃም ከጓደኛዬና አባሪዬ አንደኛ ተከሳሽ፣ ሶልያና ሽመልስ (ክሷ In Abesntia) እየታየ ያለችና በአንድ ቀጠሯችን ፖሊስ Interpol ጋር በመሆን ለመያዝ ጥረት እያደረገ እንደሆነ የገለፁት በጥብቅ የምትፈለግአሸባሪቤት በሌለችበት ፖሊስ ላደረገው ብርበራ ማቀዝቀዣ  Fridge ዙሪያአገኘሁትያለው ግንቦት ሰባት የተባለ ፓርቲ በታህሳስ 2005 የወጣ የአባላት የውስጥ Newsletter ቀኑ በሰነዱ ላይ ያልተመለከተ ሌላ የዚሁ ፓርቲ ሰነድ ነው፡፡

ውዴ ለመረጃ አንች ከእኔ ትቀርቢያለሽና ከላይ ስለጠቀስኩትሰነድጉዳይ ብዙ ሰምተሻል የሚል ግምት አለኝ፡፡ እኔ ያለኝን መረጃ እና የዚህ ሰነድ ስለክስ ሒደቱ ሊኖረው ስለሚችለው አመላካችነት አንዳንድ ወሬዎችን እያመጣን እንተክዝ እስኪ፡፡

መቼም አሜሪካ ግሩም ሀገር ነው፡፡ ብዙ ነገሮች እንደቅሌት (Scandal) እየሆኑ ሲወጡ የምናይበት የቅሌቶች ሁሉ ቅሌት ድሞ Richard Nixon ነው   ‘The Watergatge scandal’ ይሉታል፤ ኒክሰን 1972 ለተደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መረጃ ለማግኘት በማሰብ Washington DC የሚገኘውን የዲሞክራቲክ ፓርቲ ICT ዋና መሥሪያ ቤት Watergate የተባለው ሕንፃ ውስጥ) እንዲበዘበዝ በማስደረጋቸውና ይሄም ድርጊታቸው በፕሬሱ ይፋ በመሆኑ ኒክሰን ከስልጠናቸው ተዋርደው እንዲለቁ ሆነ፡፡

Watergate ብዝበዛን ተከትሎ ብዙ ሐረጎች ለብዙ ሁነቶች መግለጫ በመሆን ይቀርቡም ጀመር ለምሳሌ ‘The Watergate Burglars’ ‘The Saturday Night Massacre:- ‘United States Vs Nixon’…. (የእያንዳንዷን ዝርዝር Google እያደረግሽ እንደምታይው ተስፋ አለኝ አበባዬ)፡፡ ከዛም በኋላ የተለያዩ ቅሌቶችን Watergate ጋር እያያያዙ መጥራት የተለመደ ነው፡፡ አሁንም ሌላ ምሳሌ  ‘The Monicagate’ የፕሬዚዳንት ክሊንተንን የወሲብ ቅሌት ለመግለጽ)( ‘The Nipplegate’ (2003 . ጃኒት ጃክሰን Live የቴሌቪዥን የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ባልታሰበ ሁኔታ ያጋጠማትን የጡት ጫፍ (Nipple) መራቆትና በቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ታሪክን የቀየረ ሁነት ለመግለፅ)

ይሔን ሁሉ ማለቴ ወዴት ለመሔድ አስቤ እንደሆነ ሳትረጂው አትቀሪም ፍቅር፡፡ ከላይ ወደጠቀስኩልሽ ግንቦት 7 የተባለ ፓርቲ ሰነድ ጓደኛችን ቤት ተገኝ ስለመባሉ ጉዳይ ላስረዳሽ አስቤ ነው፡፡ ተገኘ የተባለው ሰነድ ላይ ጓደኛችን ወክለው ቤቷን ሲያስፈትሹ የነበሩት እናቷይህ ሰነድ ፖሊስ ከፋይሉ ጋር ይዞት የመጣው ሰነድ ነው፡፡ እዚህ ቤት የተገኘ አይደለምና እዚህ ቤት ተገኘ ብዬ ልፈርም አልችልምማለታቸው በሰነዱ ላይ በግልጽ የተመለከተ ሲሆን፤ ሰነዱ ተገኘ የተባለበት ቦታ ደግሞ የጉዳዩን አስገራሚነት ያንረዋል- ማቀዝቀዣ (Fridge)!  (በነገራችን ላይ ፖሊስ የወንጀልማስረጃከውጪ ይዞ ቤት ውስጥ በመጣል ‘Eureka’ ‹ማስረጃአገኘሁ የሚልበት ልማድ አዲስ አይደለም፤ በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ጉዳይ የተከሰሱ ብዙ ሰዎች የዚህ ዓይነትፖሊስ አመጣሽማስረጃዎች ሰለባ መሆናቸውን እያነበብን/እየሰማን ነው የጎለመስነው፡፡ ፖሊስን ወደቤታቸው ፈትሸው ከማስገባት ጀምሮ የተለያዩ ፖሊስን የመጠበቅ አስቂኝ ተግባራትን በቤት ብርበራ ወቅት እንደሚያከናውኑ ስንለውም ኖረናል፡፡ አስቢው እስኪ ውዴ፤ ሕዝብ ፖሊስን ሲጠብቀው የሚኖርበት ሀገር!)

ለማንኛውም ይህ ‹ Fridge ማስረጃ› ‹አገኘሁየሚለው የፖሊስ ተግባር ነው… ‘The Fridgegate Scandal’ እንድል ያደረገኝ፡፡ እስርም፣ ክስም፣ማስረጃም›…. ከአሳሪዬ በኩል መምጣቱፍርድምከአሳሪዬ በኩል ሊመጣ ይችላል የሚል ስጋት ውስጥ ቢከተኝም ተስፋ አልቆርጥም! ወዳጄ ‘The Fridgegate scandalእንደ አንድ የክስ ሒደቱ ማሳያ ማቅረቤ ‘The Fridgegate Burgalrs’ ለፍትሕ ይቀርባሉ ብዬ በማሰብ አይደለም ወይም በባለስልጣኖቻችን መካከል ‘The Renaissance Massacre’ ተከስቶ ስልጣን ይለቃሉ የሚል ቅዠትም የለኝም፤ይልቁንም (በክርክሩ ሒደት የምናየው ቢሆንም) የቀረቡብን የሰነድ ማስረጃዎች አስቂኝነትና ምን እንደሚያስረዱ ካለመታወቃቸው አልፎ እንዲህ የአሳሪዎቻችን የቅሌት ተግባራት ውጤት መሆናቸውን Alexander Hamilton Federaliot Paper Number 78:

“The Judiciary is ‘beyond comparison the weakest of the three department of power”
ቃል ጋር አንድ ላይ ስመለከተውማስረጃፈጣሪውእና ጠንካራው አሳሪያችንደካማውንፍርድ ቤት እንዳይጫነው ብሰጋ ነው፡፡ ቢሆንም ግን ሁሌም ተስፈኛ ነኝ፡፡ ማሬ በሕግ ቋንቋ (በልሳን) ትንሽ አውርተን ወደ ሌላ ጉዳያችን እንሂድ፡፡ ያን ረጅም የምርመራ ሂደት አልፈንና ሕግ-አስፈፃሚው ሂደቱን እንዲያስጠብቁ በሕግ-አውጭው የወጡትን የስነ-ስርዓትና መሰረታዊ የመብት መጠበቂያ (Procedual and substantive) ሕጎችን አንድ በአንድ እየሰባበረ ለሕግ ተርጓሚው አካል ያቀረባቸውንየወንጀል ድርጊት ማሳያ ማስረጃዎችንበሕግ ትምህርት ቤት ‘The Fruits of Poisonous free’ የተባሉት ሲሆኑ፤ ተስፋዬም ከሶስቱ የመንግሥት አካላት ደካማ የተባው ሕግ ተርጓሚው አካል የቀረበለት ነገር በትክክልፍሬእንዳልሆነ ይገነዘባል የሚል ሲሆን፤ ካልሆነምፍሬውከተመረዘ ዛፉ ለሕግ ተርጓሚው አካል በግድ ካልገመጥ አይለውም አይባልም፤ ዛፉን ለመመረዝ አካል ፍሬውን ለማስገመጥ አይሰንፉምና፡፡ ፍቅር! ለማንኛውም ተስፋ ጥሩ ነው፡፡

መንግስቱ ኃይለማርያም ደሳለኝን (MHD) አየኋችሁ

የኔ እመቤት! እውነት እውነት እልሻለሁ እንደ መታሰር ያለ አስተውሎትን የሚያሳድግ ነገር የለም፡፡ ምክንያቴን ከነማስረጃዬ አቀርባለሁ፡፡ ያኔ በዞን ዘጠኝ እያለሁ (ከመታሰሬ በፊት) ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን አጠር አድርገን ‘HMD’ በሚል አፅርሆት እንጠራቸው ነበር፡፡ መታሰሬ ግን ዓይኔን አበራልኝና የእስከዛሬው አጠራራችን የፊደል መፋለስ እንዳለበት ለመረዳት ችያለሁ፡፡ እንዴት?

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለሽብር፣ ስለእስርና ስለመንግስታቸው አቋም በቅርቡ ተጠይቀው የሰጡትን ምላሽ በኢቲቪ ተመለከትኩ፡፡ ‹‹እነዚህ አሸባሪዎች ከአስመራ እስከ ሞቃዲሾ የተዘረጋው የሽብር ሰንሰለት አካላት ናቸው (በነገራችን ላይ በቅርቡ የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ከደቡብ ሱዳን ጁባ ተይዘው መምጣታቸውን ተከትሎ የሽብር ሰንሰለቱ ከአስመራ-ሞቃዲሾ-ጁባ ተለጥጦ ሶስት ማዕዘን መስራቱን መንግስት እየገለፀ ነው) ጋዜጠኛ ነኝ፣ ብሎገር ነኝ እያሉ የሽብር ዓላማን ማንገብ አይቻልም፡፡ እናንት ጋዜጠኞችም ተጠንቀቁ….›› አይነት ዱላ ቀረሽ ዛቻ ሲያሰሙ ተመልክቼ እንደሰውየውኃይለማርያም አሁንስ መንግስቱን መንግስቱን መሰልከኝ ማለቴ አልቀረም፡፡ ለዛም ነው ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መንግስቱ ኃይለማርያም ደሳለኝን (MHD) የሚለውን ስያሜ አፌ ላይ አልጠፋ ያለው፡፡

እንደዱሮውይሄ በፍርድ ቤት የተያዘ ጉዳይ ስለሆነ አስተያየት መስጠት አልፈልግምማለት ቀረና እንደዳኛ ግራና ቀኝ የተቀመጡትን ጋዜጠኞች እየገላመጡ ቢሯቸው ውስጥ ፍርድ ስጡኝ፡፡ ሌላው ሁሉ ይቅር በሕግ ፊት ነፃ ሆኖ የመገመት ሕገመንግስታዊ መብቴን ያክብሩ አላልኩም፡፡ ባይሆን የቀረበብኝንማስረጃተመልክተው ፍርድዎችን ይስጡም አልልም፡፡ ግን ግንለባንዲራ ፕሮጀክታችን› (የሕዳሴው ግድብ) ማሰሪያ ይሆን ዘንድ የሁለት ወር ደመወዜን ለቦንድ መግዣ (ምንም እንኳን ለቦንድ ግዢ ጠቅላላ ክፍያ ሳልጨርስ ከስራ በመሰናበቴ ምክንያት ደመወዜ ቢቋረጥም) መስጠቴን እንደውለታ ቆጥረው በቤተ-መንግስት የዘረጉትየፍርድ ችሎትላይ ምህረት ቢያደርጉልኝ ምን አለ? ‹ወርቅ ላበደረ ጠጠር፣ እህል ላበደረ አፈርይሰጡታልን?
ውቤ! ለማንኛውም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተበየነብንን የሽብርተኝነት ካባ በፍርድ ቤት እንደማይፀናብን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

የነሲቡ ችሎት

አፈ ንጉስ ነሲቡ መስቀሉ 1874 . ጀምሮ ወደ 30 ዓመት ለሚሆን ጊዜ በዳኝነት የተለያዩ የኢትዮጵያን ነገስታት ያገለገሉ ሲሆን ፍርዳቸው እጅግ ከባድና ጠንካራ ስለነበር በዘመኑእባክህ ከነሲቡ ፊት አታቁመኝእየተባለ ይለመን እንደነበር መርስኤ ሀዘን ወልደቂርቆስ በዓይን ያዩትን፤ በጆሮ የሰሙትን፤ ከትበው ይነግሩናል፡፡ በተመሳሳይ ጉዳይ በንጉሱ ዘመን አርሲ፣ አሰላ ላይ እጅግ ጨካኝ ደኛ ተሹመው ፍርዳቸው ከባድ ከመሆኑ የተነሳአቤት አቤት፤ የአሰላው ፍርድ ቤትእስከመባል ደርሶ እንደነበር አሁንም ማስረጃችን ታሪክ ነው፡፡

ውዴ! ይሔን የምፅፍልሽ የእኛው ዘመንንየነሲቡ ችሎትአስመለክቶ ትንሽ ነገር ብዬሽ ደብዳቤዬን ልቋጭልሽ በማሰብ ነው፡፡ አዋጅ ቁጥር 652/2001 (የፀረ-ሽብር አዋጅ) ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በሽብር ጉዳዮች ላይ ስልጣን (Juridiction) ያለው የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት እንደሆነ በመደንገጉ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ተኛ ወንጀል ችሎት የተለያዩ በፀረ-ሽብር ሕጉ የተከሰሱ ግለሰቦችንና ቡድኖችን ጉዳይ እያየ የቆየ ሲሆን፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞየፀረ-ሽብር ሕጉ ሰለባዎችእየተበራከቱ በመሔዳቸው ምክንያት 4ተኛውን ወንጀል ችሎ ለማገዝ በማሰብ 19 ወንጀል ችሎ የሽብር ጉዳዮችን በማዬት ላይ ይገኛል፡፡

በፀረ ሽብር ሕጉ ተከሰውኖ 4ተኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ነፃ የወጡ (Acquit) ሰዎች ብዛት ለጊዜው ለማወቅ ባልችልም እጅግ በጣም ትንሽ እንደሆኑ ግን እርግጠኛ ነኝ፡፡ ይህ የሆነው ችሎቱ ከሌሎች ችሎቶች የተለየ በመሆኑ እንዳልሆነም አስባለሁ፡፡ ይልቁንም ችሎቱ የሚይዛቸው ጉዳዮች በፀረ-ሽብር ሕጉ አግባብ ለማየት ስለሚገደድ ነው፡፡ መቼም የፀረ-ሽብር ሕጉን አሳፋሪነትና ጅምላ ጨራሽነት ላንች እንዳዲስ በመንገር ጊዜሽን አላባክንብሽም፡፡ ለዛም ነው በዚህ ዘመንእባክህ 4ተኛ ወንጀል ችሎት ፊት አታቁመኝወይምአቤት አቤት፣ 4ተኛው ወንጀል ችሎትብንል ብዙም የማያስገርመው፡፡ የፀረ-ሽብር ሕጉ ከሚሰጠው ሰፊና ጠቅላይ የሆነ የወንጀል ትርጉም አንፃር ከልብ ወለዳዊው ‘Moratorium on the Brain’ አዋጅ ጋር በተነፃፃሪ መቆም የሚችል ከመሆኑም በላይ በሽብር ጉዳይ የተሰየወን ችሎትም እጅግ አሳፋሪ ያደርገዋል፡፡

እንግዲህ የእኛም ጉዳይ 4ተኛ ወንጀል ችሎት እህት ከሆነው 19ነኛ ወንጀል ችሎት እየታዬ የሚገኝ ሲሆን የፀረ-ሽብር ሕጉምሰለባፍለጋ በችሎታችን ተገኝቷል፡፡ እንግዲህ አበባዬ ጉዳያችን በፀረ-ሽብር ሕጉ ከመታየቱ ጋር ተያይዞ ስራ አስፈፃሚው አካልማስረጃፈጥሮ የከሰስን መሆኑ ነው ችሎቱንየነሲቡ ችሎትያደረገው፡፡ ለማንኛውም ግን ይሄን ስታነቢ ታዲያከአንበሳ መንጋጋ፣ ማን ያወጣል ስጋብለሽ ተስፋ እንደማትቆርጪ አምናለሁ፡፡ እኔና አንች እኮ ተሸንፈን አናውቅም ውዴ፡፡ ሁሌም ማሸነፍ፣ ሁሌም ሌላ ተስፋ ማድረግ፣ ሁሌም ደስተኛ መሆን፣ ሁሌም መዋደድ የሕይወት ግባችን አይደለምን ? ታዲያ ይችን ክስ በድል እንዳንወጣት ማን ያግደናል? ምን አልባት አሳሪያችን፡፡ Hamilton በድጋሚ ጠቅሼልሽ ተስፋችንን አለምልመን እንለያይ፡

‘The Judiciary (…) has no influence over either the sword or the purse (…) It may truly be said to have neither force nor will, but merely judgement’


Amen!